በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሦስት ሰዓታትን በፈጀ ስኬታማ ቀዶ ጥገና 10 ኪሎግራም ዕጢ ተወገደ

ሰብስክራይብ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሦስት ሰዓታትን በፈጀ ስኬታማ ቀዶ ጥገና 10 ኪሎግራም ዕጢ ተወገደ

በክልሉ በሚገኘው ሙዱላ ሆስፒታል፤ በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ነዋሪ ለሆነችው የ34 ዓመት ሴት በስምንት የሐኪሞች ቡድን አባላት ህክምናው በተሳካ ሁኔታ መከናወኑ  ታውቋል።

ታካሚዋ በዕጢው ሳቢያ ላለፉት 10 ዓመታት በጀርባዋ ተኝታ እንደማታውቅና እንደልብ ተንቀሳቅሳ ሥራ መሥራት እንደማትችል የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።

ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ሙዱላ ሆስፒታል መሰል ቀዶ ሕክምና ሲያከናውን ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነ ተገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0