ሊቢያ በኪየቭ ጥቃት የተጎዳውን የሩሲያ ጋዝ ጫኝ መርከብ ለመረከብ ውል ተፈራረመች

ሰብስክራይብ

ሊቢያ በኪየቭ ጥቃት የተጎዳውን የሩሲያ ጋዝ ጫኝ መርከብ ለመረከብ ውል ተፈራረመች

የስምምነቱ አላማ በየካቲት መጨረሻ በዩክሬን የካሚካዜ ድሮን ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባትንና ከቁጥጥር ውጪ የሆነችውን ‘አርክቲክ ሜታጋዝ’ የተሰኘችውን የሩሲያ የነዳጅ ጫኝ መርከብ ኃላፊነት ለመረከብ ነው።

መርከቧ በአሁኑ ወቅት በነፋስና በባሕር ሞገድ ምክንያት ቀስ በቀስ ወደ ሊቢያ የባሕር ዳርቻ እየተንሳፈፈች ትገኛለች።

የሊቢያ ብሔራዊ የነዳጅ ኮርፖሬሽን፤ ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ጫኝ መርከቧ በአካባቢው ሥነ-ምህዳር ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ ወደ ሊቢያ ወደብ እንድትጎተት ይደረጋል ሲል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ብሔራዊ የነዳጅ ኮርፖሬሽኑ ጉዳት ከደረሰባቸውና የባሕር ብክለት ሊያስከትሉ ከሚችሉ መርከቦች ጋር በተያያዘ ድንገተኛ ምላሽ በመስጠት ረገድ ለሚሠራ ዓለም አቀፍ ኩባንያ ውሉን ሰጥቷል፡፡ ተግባራዊ ሥራው ከጣሊያኑ ‘ኤኒ’ ኩባንያ ጋር በመተባበር ‘ሜሊታ ኦይል ኤንድ ጋዝ’ በተሰኘው የኮርፖሬሽኑ ቅርንጫፍ ይከናወናል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0