አፍሪካ ጨዋታውን ቀይራለች፦ ከሀብት ማውጫ ክልል ወደ ኢንዱስትሪ ማዕከልነት - የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
21:01 21.03.2026 (የተሻሻለ: 21:04 21.03.2026)
ሰብስክራይብ
አፍሪካ ጨዋታውን ቀይራለች፦ ከሀብት ማውጫ ክልል ወደ ኢንዱስትሪ ማዕከልነት - የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
የዓለም የወሳኝ ማዕድናት ስትራቴጂዎች ትኩረታቸው ከአፍሪካ ጥሬ ዕቃዎችን ማውጣት ነው። ደቡብ አፍሪካ ግን በቡድን 20 ሊቀመንበርነቷ ይህንን በመቃወም ማዕድናት ምንጫቸውን ተጠቃሚ እና በኢንዱስትሪ ማልማት እንዳለባቸው ተሟግታለች ሲሉ ሮናልድ ላሞላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
አፍሪካ ጥሬ ዕቃ መላክ ብቻ ሳይሆን፤
ሀብቶቿን በማቀነባበር ያለቁ ወይም በከፊል ያለቁ ምርቶችን ለዓለም ገበያ ማቅረብ እንድትችል የክህሎት እና የፋይናንስ ድጋፍ ያስፈልጋታል ብለዋል።
የደቡብ አፍሪካ የልማት ማኅበረሰብ ሰፊ የማዕድን ሀብት በተለይም 70% የሚሆነውን የዓለም የሊቲየም እና የፕላቲነም ቡድን ብረቶች እንደሚሸፍን ጠቅሰው፤ ከቀረጥ ውጪ የሆኑ እንቅፋቶችን ማስወገድ የወቅቱን ክልላዊ ንግድ (21%) የበለጠ በማሳደግ የደቡባዊ አፍሪካን የጋራ ዕድገት እንደሚያጎለብት አፅንዖት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X