ደቡብ አፍሪካ በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሰብዓዊ መብቶች ትቆማለች - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
20:03 21.03.2026 (የተሻሻለ: 20:04 21.03.2026)
ሰብስክራይብ
ደቡብ አፍሪካ በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሰብዓዊ መብቶች ትቆማለች - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
የሰብዓዊ መብቶች ቀን ሁለት ዋና ዋና ቃል ኪዳኖችን የያዘ ነው፡፡ ይኸውም በሕገ-መንግሥቱና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር መሠረት ደቡብ አፍሪካውያን በሀገራቸው ለመብቶቻቸው የሚቆሙበት እና ሀገሪቱ በዓለም መድረክ ላይ በነፃነት የመናገር መብቷን የምታስከብርበት መሆኑን ሮናልድ ላሞላ ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት በጆሃንስበርግ "ለሉዓላዊነት እና ዲሞክራሲያዊ ድሎች የመቆም ሕዝባዊ ሰልፍ" ላይ ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት ቃለ ምልልስ ነው።
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ህዳጣንን ጨምሮ ለሁሉም ዜጎች ጥበቃ ከሚያደርገው ሕገ-መንግሥት እንደሚቀዳ እና ዓለም አቀፍ ቀውሶች ሀገርን በሚያንኳኩበት ወቅት የመንግሥትን እርምጃ እንደሚመሩ ገልጸዋል።
ለምሳሌ በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ መስተጓጎል እና በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት ምክንያት የነዳጅ ዋጋ ሲጨምር፤ መንግሥት ተራውን የደቡብ አፍሪካ ዜጋ ከጫናው ለመታደግ እና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪን ለመከላከል ጣልቃ እየገባ መሆኑን ዲፕሎማቱ ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X