4 የቤኒን የነሐስ ቅርሶች ወደ ናይጄሪያ ሊመለሱ ነው - ለአፍሪካ ቅርስ ሌላኛው ድል
19:40 21.03.2026 (የተሻሻለ: 19:44 21.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
4 የቤኒን የነሐስ ቅርሶች ወደ ናይጄሪያ ሊመለሱ ነው - ለአፍሪካ ቅርስ ሌላኛው ድል
የዙሪክ ዩኒቨርሲቲ በሰው ልጅ ጥናት ሙዚየሙ የሚገኙትን እነዚህን ቅርሶች ለናይጄሪያ ለመመለስ ተስማምቷል። ይህም የናይጄሪያ ብሔራዊ የሙዚየሞች እና ሀውልቶች ኮሚሽን እ.ኤ.አ በመጋቢት 2024 ቅርሶቹ እንዲመለሱ ይፋዊ ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ የመጣ ነው። ቅርሶቹ ከጥቂት ወራት በኋላ በሌጎስ ወደሚገኘው የናይጄሪያ ብሔራዊ ሙዚየም ይተላለፋሉ።
ከረጅም ጊዜ መዘገየት በኋላ የሚመለሰው ቅርስ
የኮሚሽኑ ዋና ዳይሬክተር ኦሉግቢሌ ሆሎዌይ፤ ቅርሶቹ መመለሳቸው "ያለፈውን የቅኝ አገዛዝ ጠባሳ ለመፈወስ" የሚረዳ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። የቤኒን ሕዝብና መላው ናይጄሪያውያን የቅርሶቹን መመለስ ትልቅ የተምሳሌት ዋጋ እንደሚሰጡትም ጠቁመዋል።
ታሪካዊ ዳራ
እነዚህ የጥበብ ሥራዎች እ.ኤ.አ 1897 በእንግሊዝ ወታደሮች ከቤኒን ንጉሣዊ ቤተ-መንግሥት ተዘረፈው በሥነ-ጥበብ ገበያ አማካኝነት በዓለም ዙሪያ ተበታትነው ቆይተዋል። ጥናቶች አንዳንዶቹ የነሐስ ቅርሶች የተሠረቁት በአትላንቲክ የባሪያ ንግድ ወቅት እንደሆነ ይፋ አድርገዋል፡፡ ይህም በቅኝ አገዛዝ ዘመን የአፍሪካውያን ሕይወት እና ጥበብ እንዴት ይበዘበዝ እንደነበር ማሳያ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X