እስራኤል ዓለም አቀፍ ሕግን በመጣስ የባለብዙ ወገን ግንኙነትን አደጋ ላይ ጥላለች - የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
18:01 21.03.2026 (የተሻሻለ: 18:07 21.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
እስራኤል ዓለም አቀፍ ሕግን በመጣስ የባለብዙ ወገን ግንኙነትን አደጋ ላይ ጥላለች - የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ዓለም አቀፉ የፍትሕ ፍርድ ቤት የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለማስቆም ሦስት ጊዜ ውሳኔ ቢያስተላልፍም፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ባላቸው የእስራኤል ወዳጆች ምክንያት "እያቃሰተ" እና "ተዝለፍልፎ" እንደሚገኝ ሮናልድ ላሞላ ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት ልዩ ቃለ ምልልስ ገልጸዋል።
ይህ ሥርዓታዊ ውድቀት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የዓለም አቀፉ የፍትሕ ፍርድ ቤት እና የዓለም አቀፉን የወንጀል ፍርድ ቤት ተዓማኒነት በከፍተኛው እንደሸረሸረ ሚኒስትሩ ሞግተዋል። እነዚህ ዓለም አቀፍ ተቋማት በጊዜ ሂደት ዓለም አቀፍ ግጭቶችን የመፍታት አቅማቸው እየተዳከመ መምጣቱን አስረድተዋል።
ደቡብ አፍሪካ የደረሰባትን ጭቆና ለማስቆም ለረዳት ዓለም አቀፍ ትብብር ክብር ለመስጠት የፍልስጤማውያንን ትግል እንደምትደግፈ ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።
"ፍትሕ በጎደለበት ሁሉ ከሰብዓዊ መብቶች እና ከዓለም አቀፍ ሕግ ጋር እንወግናለን " ሲሉ ላሞላ ደምድመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X