የሳዑዲ አረቢያ ግዙፍ የፎስፌት ማዳበሪያ አምራች ማድን 50 ሺህ ቶን ዳፕ ማዳበሪያ ለኢትዮጵያ መሸጡን አስታወቀ

ማዳበሪያ
ማዳበሪያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.03.2026
ሰብስክራይብ
የሳዑዲ አረቢያ ግዙፍ የፎስፌት ማዳበሪያ አምራች ማድን 50 ሺህ ቶን ዳፕ ማዳበሪያ ለኢትዮጵያ መሸጡን አስታወቀ

ማዳበሪያው በአንድ ቶን ከ800 እስከ 850 ዶላር ተግዝቷል የተባለ ሲሆን ከሳዑዲ አረቢያ ያኑቡ ወደብ ተነስቶ በጂቡቲ በኩል እንደሚገባ ታውቋል።

ጭነቱ በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ ላለመላፍ የተለመደውን የሳዑዲ አረቢያ የምስራቅ ዳርቻ ወደብ ራስ አል-ካሂር በመተው በቀይ ባሕር በኩል አድርጎ ይጓጓዛል ተብሏል፡፡

ማድን እስከ ጂቡቲ ድረስ ያለውን የጉዞ ወጪ የሚሸፍን ሲሆን ቀጣዩን ሂደት ገዢው የኢትዮጵያ መንግሥት እንደሚችል ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0