‘የፀረ-አፓርታይድ ማንነት’ የደቡብ አፍሪካን የዓለም አቀፍ ሕግ ቁርጠኝነት ቀርጿል - ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን ሮናልድ ላሞላ

ሰብስክራይብ

‘የፀረ-አፓርታይድ ማንነት’ የደቡብ አፍሪካን የዓለም አቀፍ ሕግ ቁርጠኝነት ቀርጿል - ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን ሮናልድ ላሞላ

መጋቢት 12 (March 21) የሚከበረውን የደቡብ አፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች ቀን ዋዜማ ምክንያት በማድረግ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ልዩ ቃለ ምልልስ ያደረጉት የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማት፤ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በፀረ-አፓርታይድ ታሪክ ላይ ተመሥርቶ ዓለም አቀፍ አንድነትን እንደሚመዝ ተናግረዋል።

የሁሉንም ሀገራት እኩል ሉዓላዊነት የሚያረጋግጠው የተባበሩት መንግሥታት ቻርተር አንቀጽ 2፤ የደቡብ አፍሪካን የሰላም ተነሳሽነት፣ የውይይት ጥረቶች እና አለመግባባቶችን በዓለም አቀፍ ትብብር አማካኝነት የመፍታት ቁርጠኝነት እነደሚመራ ገልጸዋል።

የደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፋዊ አቋሞች በሕገ-መንግሥቱ፣ በውጭ ፖሊሲ ሕግ እና ብሔራዊ ጥቅም ላይ እንደተመሠረቱ አጽንኦት ሰጠተዋል። በሉዓላዊነት ጉዳዮች ላይ የተባበሩት መንግሥታት ቻርተር ለደቡብ አፍሪካ ዋነኛ መመሪያ ሆኖ እንደሚያገለግል ግልፅ አድርገዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0