ፖላንድ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ጽጌ ዱጉማንና ሦስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን ቪዛ ከለከለች

ፖላንድ
ፖላንድ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.03.2026
ሰብስክራይብ
ፖላንድ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ጽጌ ዱጉማንና ሦስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን ቪዛ ከለከለች

በ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ በሴቶች 800 ሜትር የብር ሜዳሊያ በማሸነፍ በታሪክ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት እና ሌሎች የመካከለኛ ርቀት ሯጮች ሳሮን በርሄ፣ ሀረገወይን ካላዩ እና ሞሲሳ ስዩም በፖላንድ ቶሩን እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንዳይሳተፉ ታግደዋል።

የፖላንድ የቪዛ እገዳ ባሳለፍነው ጥር ወር በፍሎሪዳ ታላሃሲ ተዘጋጅቶ በነበረው የዓለም አትሌቲክስ የታዳጊዎች ሻምፒዮና ውድድር 14 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ከተከለከሉ በኋላ የመጣ ነው፡፡

እነዚህ ክልከላዎች ኢትዮጵያ ሜዳሊያ የምታገኝባቸው ውድድሮች እንዲቀንሱ የሚያደርጉ እና "ስፖርታዊ አፓርታይድ" እንደሆኑ የዘርፉ ባለሙያዎች አሳስበዋል፡፡

ኢትዮጵያ በፖላንድ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በስድስት አትሌቶች ብቻ ተወክላለች።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0