መንግሥት ከተወረሰ ሕገ-ወጥ ነዳጅ ሽያጭ ከ48.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ እንዳገኘ ገለጸ

Minister of Trade and Regional Integration
Minister of Trade and Regional Integration - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.03.2026
ሰብስክራይብ
መንግሥት ከተወረሰ ሕገ-ወጥ ነዳጅ ሽያጭ ከ48.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ እንዳገኘ ገለጸ

በስድስት ክልሎችና በሁለት የከተማ አስተዳደሮች በተደረገ የተቀናጀ ዘመቻ ከ448 ሺህ ሊትር በላይ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ነዳጅ መወረሱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

በተደረገው ክትትል በአጠቃላይ 250,221 ሊትር ቤንዚን እና 198,432 ሊትር ናፍጣ በሕገ-ወጥ መልኩ ሲዘዋወር እና ጥቅም ላይ ሲውል ተይዞ ተወርሷል ሲሉ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ በማኅበራዊ ገጻቸው ገልጸዋል።

የንግድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የቡድን መሪዎች፣ የነዳጅ ማደያ ባለቤቶችና ሠራተኞች እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የጸጥታ አካላትን ጨምሮ በሕገ-ወጥ ንግድና አሻጥር ተሳትፈው የተገኙ 613 ሰዎች ታስረዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0