ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ በደቡብ ኦሞ ዞን 496 በላይ እንስሳትን ገደለ
በሽታው የተከሰተው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ማሌ ወረዳ ሥር በሚገኙ ቲኪቦኮ እና ቡላንሳ በተባሉ ቀበሌዎች ውስጥ እንደሆነና ባለፉት ሁለት ቀናት የሞት ቁጥሩ እየጨመረ መምጣቱ የአካባቢውን አርብቶ አደር ማኅበረሰብ እንዳሳሰበ የአካባቢውን የቀይ መስቀል ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
የበሽታውን መንስኤ በትክክል ለማወቅ የክልሉ የጂንካ ማዕከልና የዞኑ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች በጋራ ጥናት እያካሄዱ ሲሆን ከሞቱ እንስሳት ናሙና ተሰብስቧል፡፡
ሞቱ የሚቀጥል ከሆነ ኑሮው ሙሉ በሙሉ በእንስሳት እርባታ ላይ የተመሠረተው የአርብቶ አደሩ ማኅበረሰብ የከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ ሊደርስበት እንደሚችል የተናገሩት ኃላፊው፤ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የመድኃኒት፣ የክትባትና የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X