በመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ወቅት አፍሪካ ከዓለም አቀፍ ንግድ አንጻር አስተማማኝ መጠለያ ናት - ፓን-አፍሪካዊው ነጋዴ

ሰብስክራይብ
በመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ወቅት አፍሪካ ከዓለም አቀፍ ንግድ አንጻር አስተማማኝ መጠለያ ናት - ፓን-አፍሪካዊው ነጋዴ

​ የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ መዘጋት አፍሪካን ብዙም ስለማይነካት፣ አኅጉሪቱ “ራሷን እንደ ታማኝ አጋር በማቅረብ” ተጠቃሚ ልትሆን ትችላለች ሲሉ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ሊደርሺፕ ካውንስል ተባባሪ መስራች ፐርሲ ሞራፔዲ ኮጂ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።


​“ይሁን እንጂ ከኢኮኖሚና ከንግድ አንፃር በቀጥታ ይነካናል። ይህ ደግሞ ያሉንን ሀብቶች እዚሁ አህጉር ውስጥ እሴት ጨምረንባቸዉ እንዴት መጠቀም እንደምንችል ለመመልከት ትልቅ ዕድል ነው” ሲሉ ገልጸዋል።


​ አፍሪካ በየዓመቱ 89 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ዕዳ በምትከፍልበት በዚህ ወቅት፣ የአፍሪካ ሕብረት ዋና ዓላማ ሊሆን የሚገባው በአህጉሪቱ መካከል ያለውን ንግድ ማጠናከር እንጂ የፋይናንስ ክፍተቱን ለመቀነስ እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማረጋገጥ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ማሻሻል ብቻ መሆን የለበትም ሲሉ ኮጂ አክለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0