የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጅቡቲ ውስጥ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ለመገንባት 10 ሄክታር መሬት መጠየቁ ተዘገበ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጅቡቲ ውስጥ የነዳጅ ማጠራቀሚያ
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጅቡቲ ውስጥ የነዳጅ ማጠራቀሚያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.03.2026
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጅቡቲ ውስጥ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ለመገንባት 10 ሄክታር መሬት መጠየቁ ተዘገበ

በጅቡቲ ዳመርጆግ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ሊገነባ ዕቅድ የተያዘለት ይህ ፕሮጀክት፣ በመጀመሪያው ምዕራፍ 150,000 ኩቢክ ሜትር የመያዝ አቅም ይኖረዋል ተብሏል።

የፕሮጀክቱ የግንባታ ስፍራ፣ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ዋና ማከፋፈያ እና በኢትዮ-ጅቡቲ የምድር ባቡር መስመር አቅራቢያ የሚገኝ በመሆኑ፣ ነዳጅ ከመርከቦች በቀጥታ ወርዶ በባቡር ወደ ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ስርጭት እንዲጓጓዝ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል መባሉን የግል መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ይህ ተነሳሽነት የመጣው ኢትዮጵያ እየተጠቀመችበት ያለው የ"ሆራይዘን ተርሚናልስ" የ5 ሚሊዮን ቶን የመያዝ አቅሙ በመሞላቱ አዲስ አማራጭ ግድ በመሆኑ ነው ተብሏል።

ፕሮጀክቱ በኃይል ራስን በራስ የማስተዳደር አቅሟን እንድታሳድግ እና በመርከቦች መዘግየት ምክንያት የሚከፈለውን ከፍተኛ የ"ዴመረጅ" (የማቆያ) ወጪ እንድትቀንስ ይረዳታል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0