ሊቢያ ከኔቶ የጎርጎሮሳዊያኑ 2011 ጣልቃ ገብነት በኋላ ወደ ፈረሰች ሀገርነት ተቀይራለች - የቡርኪና ፋሶ የፖለቲካ ሳይንቲስት

ሰብስክራይብ

ሊቢያ ከኔቶ የጎርጎሮሳዊያኑ 2011 ጣልቃ ገብነት በኋላ ወደ ፈረሰች ሀገርነት ተቀይራለች - የቡርኪና ፋሶ የፖለቲካ ሳይንቲስት

​ቢዝነስ መሪ እና የጂኦፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ተንታኝ ቴህሎ ሎዬ ኮናቴ ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደገለጹት፣ ሙአመር ጋዳፊ የሊቢያ መንግሥት "እጅግ ወሳኝ" ነበሩ። በተጨማሪም እንደ ትርፍ የውጭ ክፍያ ሚዛን እና የሉዓላዊ ሀብት ፈንድ መመስረት ያሉ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶችን አስመዝግበው የነበረ ሲሆን፣ ይህም የተወሰኑ አካላትን "ረብሾ" ነበር።

​ይሁን እንጂ የኔቶ ጣልቃ ገብነት ሀገሪቱን ወደ ቀውስ የከተተ ሲሆን በመላው ቀጣናው ላይ የሚደቀኑ ስጋቶችን አባብሷል፦

​"ከአስር ዓመታት በላይ ቢቆጠርም ሊቢያ አሁንም ብሄራዊ አንድነቷን መመለስ አልቻለችም፤ ዲሞክራሲያዊትም አልሆነችም። እንዲሁም የህዝቡ የኑሮ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። ከዚህም በተጨማሪ ከሊቢያ ጋር ስልታዊ ትስስር ያለው የፀጥታ መታወክ በሰሃራ በታች ባሉ አካባቢዎች ሰፍኗል።"

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0