Iran school girls - Sputnik አፍሪካ

የአሜሪካ እና የእስራኤል ጦርነት በኢራን ላይ (ከየካቲት 28 ፣ 2026 እ.ኤ.አ ጀምሮ እስከ ዛሬ)

ከድርድር ወደ ጦርነት፦ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጦርነት ጀመሩ
የካቲት 28 ቀን 2026 የእስራኤል ጦር ከአሜሪካ የታጠቁ ኃይሎች ጋር በመተባበር፣ የኢስላማዊ ሪፐብሊክ የኒውክሌር መርሃ-ግብር አበልጽጋለች በሚልክስ "ኦፕሬሽን ኤፒክ ፉሪ" የተሰኘውን ወታደራዊ ጥቃት በኢራን ላይ ከፍተዋል።
ቴህራን የኒውክሌር ስምምነቱን (NPT) በመጥቀስ መርሃ-ግብሯ ለሰላማዊ ዓላማ መሆኑን በተደጋጋሚ ስትገልጽ ቆይታለች። በተጨማሪም ዩራኒየም የማበልጸግ ሂደቱን ለማቆም እና ተቋሞቿን በዓለምአቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ(IAEA) ቁጥጥር ስር ለማድረግ ፈቃደኛ ብትሆንም፣ የመሠረተ ልማት አውታሮቿን ሙሉ በሙሉ ለማፍረስ ግን አልተስማማችም። አሜሪካ በበኩሏ "ዜሮ የኒውክሌር አቅም" እንዲኖር ጥብቅ አቋም ይዛለች።
በቤሩት ደቡባዊ ዳርቻ ዳሂዬ ውስጥ በእስራኤል የአየር ድብደባ የወደሙ ህንፃዎችን ፍርስራሽ አንድ ግለሰብ ፎቶግራፍ ሲያነሳ እሁድ መጋቢት 15 ቀን 2026 (እ.ኤ.አ) - Sputnik አፍሪካ
በቤሩት ደቡባዊ ዳርቻ ዳሂዬ ውስጥ በእስራኤል የአየር ድብደባ የወደሙ ህንፃዎችን ፍርስራሽ አንድ ግለሰብ ፎቶግራፍ ሲያነሳ እሁድ መጋቢት 15 ቀን 2026 (እ.ኤ.አ)
በቴህራን በተፈጸመ ጥቃት ሳቢያ የጭስ ደመና ወደ ሰማይ ሲወጣ ሰኞ መጋቢት 2 ቀን 2026 (እ.ኤ.አ) - Sputnik አፍሪካ
በቴህራን በተፈጸመ ጥቃት ሳቢያ የጭስ ደመና ወደ ሰማይ ሲወጣ ሰኞ መጋቢት 2 ቀን 2026 (እ.ኤ.አ)
1.
በቤሩት ደቡባዊ ዳርቻ ዳሂዬ ውስጥ በእስራኤል የአየር ድብደባ የወደሙ ህንፃዎችን ፍርስራሽ አንድ ግለሰብ ፎቶግራፍ ሲያነሳ እሁድ መጋቢት 15 ቀን 2026 (እ.ኤ.አ)
2.
በቴህራን በተፈጸመ ጥቃት ሳቢያ የጭስ ደመና ወደ ሰማይ ሲወጣ ሰኞ መጋቢት 2 ቀን 2026 (እ.ኤ.አ)

ፕሬዝዳንት ትራምፕ የወታደራዊ ዘመቻው ዓላማ የኢራን አገዛዝ የሚደቅነውን "ስጋት" ማስወገድ መሆኑን ገልጸዋል።

በጄኔቫ የተካሄደው የመጨረሻው የኢራን እና የአሜሪካ ንግግር የካቲት19 ቀን (እ.ኤ.አ) ያለ ስምምነት በመጠናቀቁ፣ ከጥቂት ቀናትበኋላ ዲፕሎማሲው በጦርነት ተተክቷል።

የመጀመሪያው የጦርነት ቀን እና የኢራን ጠቅላይ መሪ ግድያ

በካቲት 28 ቀን 2026 (እ.ኤ.አ) አምስት የኢራን ከተሞች በቦምብ ፍንዳታ ተናውጠዋል፦ እነርሱም ቴህራን፣ ኢስፋሃን፣ ቁም፣ ካራጅ እና ኬርማንሻህ ናቸው። የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ መኖሪያ ቤት በቀጥታ በተሰነዘረ ጥቃት ሙሉ በሙሉወድሟል።

እስራኤል ቀድሞ የመምታት ጥቃት ፈጽማለች። የጥቃቱ ኢላማዎችበፎርዶው፣ ናታንዝእና ኢስፋሃን የሚገኙ የኒውክሌር ተቋማት እንዲሁም የኢራን አብዮታዊ ዘብ(IRGC) ዋና መሥሪያቤቶች፣ የአየር መከላከያ ጣቢያዎች እና የወታደራዊ-ኢንዱስትሪው ስብስብ ማዕከላት ናቸው። እስራኤል ወታደራዊ ዘመቻዋን "ላየንስ ሮር" ስትል ሰይማዋለች። ሚሳኤሎቹ ወታደራዊ ኢላማዎችን ብቻ ሳይሆን የሲቪል መሠረተ ልማቶችንም መምታታቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች ወጥተዋል።

በቴህራን እምብርት በእስራኤል የአየር ጥቃት የወደመ መኖሪያ ቤት - Sputnik አፍሪካ
በቴህራን እምብርት በእስራኤል የአየር ጥቃት የወደመ መኖሪያ ቤት
በምዕራብ ቴህራን በሚገኘው የሻህራን የነዳጅ ማከማቻ ተቋም ላይ የደረሰ ፍንዳታ - Sputnik አፍሪካ
በምዕራብ ቴህራን በሚገኘው የሻህራን የነዳጅ ማከማቻ ተቋም ላይ የደረሰ ፍንዳታ
1.
በቴህራን እምብርት በእስራኤል የአየር ጥቃት የወደመ መኖሪያ ቤት
2.
በምዕራብ ቴህራን በሚገኘው የሻህራን የነዳጅ ማከማቻ ተቋም ላይ የደረሰ ፍንዳታ
አሜሪካ ከጦር መርከቦች ፣ ድሮኖች እና የሃይማርስ (HIMARS) የሮኬት ስርዓቶች በመጠቀም የ"ቶማሃውክ" (Tomahawk) ሚሳኤል ጥቃቶችን በኢራንኃይሎች ላይ ሰንዝራለች። የጥቃቱ ተሳታፊ የነበሩት ዘመናዊ የሚሳኤል መምሪያ ቴክኖሎጂ የታጠቁ የሚሳኤል አጥፊ መርከቦች የሆኑት ዩኤስኤስ ስፕሩዋንስ፣ ዩኤስኤስ ፍራንክ ኢ. ፒተርስን እንዲሁም ዩኤስኤስ ሚሊየስ ኢራንን ኢላማ አድርገዋል። በአጠቃላይ የአሜሪካ መርከቦች በመጀመሪያዎቹ ሁለት የጦርነት ቀናት እስከ 200 የሚደርሱ የቶማሃውክ ሚሳኤሎችን ተኩሰዋል። በኢራን አየር መከላከያ የመከኑ ሚሳኤሎች ብዛት ግን በይፋ አልታወቀም።
ኔታንያሁ በኢራን ላይ የተከፈተውን ዘመቻ በ"ደጎቹ" (እራሳቸውን እና ትራምፕን ማለታቸው ነው) እና በ"ክፉዎቹ" (ኢራን) መካከል የሚደረግ ትግል እንደሆነ ገልጸውታል። የእስራኤሉ መሪ አክለውም የአሜሪካ እና የእስራኤል ጥቃት "ጀግናው የኢራን ሕዝብ እጣ ፈንታውን በእጁ እንዲጨብጥ" እና በአገሪቱ ውስጥ የሥልጣን ለውጥ እንዲመጣ ይረዳል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።
በፍሎሪዳ  በሚገኘው ማር-አ-ላጎ በተካሄደ የጋዜጣዊ መግለጫ ማጠቃለያ ላይ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋር የእጅ ሰላምታ ሲለዋወጡ ፣ ሰኞ ታህሳስ 29 ቀን 2025 (እ.ኤ.አ) በ ፓልም ቢች ፣ ፍላ  - Sputnik አፍሪካ
በፍሎሪዳ በሚገኘው ማር-አ-ላጎ በተካሄደ የጋዜጣዊ መግለጫ ማጠቃለያ ላይ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋር የእጅ ሰላምታ ሲለዋወጡ ፣ ሰኞ ታህሳስ 29 ቀን 2025 (እ.ኤ.አ) በ ፓልም ቢች ፣ ፍላ
"ኦፕሬሽን ትሩ ፕሮሚስ-4"
የኢራን አብዮታዊ ዘብ (IRGC) "ኦፕሬሽንትሩ ፕሮሚስ-4" የተሰኘ የአጸፋ ጥቃት መጀመሩን አረጋግጧል። ይህ የአጸፋ እርምጃ በባህሬን፣ ጆርዳን፣ኳታር፣ ኩዌት፣የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እና ሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ የአሜሪካ እና የእስራኤል ወታደራዊ ተቋማትን ኢላማ ያደረገ ሲሆን።
የኢራን የአጸፋ እርምጃ ፡ በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥቃቶች ላይ የወሰደችው ጠንካራ መልሶ ማጥቃት

ዒላማዎቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

በሃይፋ የሚገኘው የእስራኤል የባህር ኃይል እና የራማት ዳዊት የአየር ኃይል ጣቢያ፤

በባህሬን የሚገኘው የአሜሪካ 5ኛ የባህር ኃይል ክፍለ ጦር ዋና መሥሪያ ቤት፤

በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የሚገኘው የዱባይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ ልማት እና የጄበል አሊ ወደብ (በጥቃቱ ምክንያት እሳት ተቀስቅሷል)፤

በኩዌት የሚገኙ ተቋማት(በዚህ ጥቃት ሦስት የአሜሪካ ወታደሮች ተገድለዋል።)

የኢራን ሚሳኤሎች በመካከለኛው ምስራቅ የሚደርሱበትን ርቀት የሚያሳይ ካርታ - Sputnik አፍሪካ
የኢራን ሚሳኤሎች በመካከለኛው ምስራቅ የሚደርሱበትን ርቀት የሚያሳይ ካርታ
እንደ ሚዲያ ዘገባዎች ከሆነ፣ በእስራኤል ላይ በተሰነዘረው "የመጀመሪያው የጥቃት ማዕበል" ቢያንስ 80% የሚሆኑት የኢራን ሚሳኤሎች ኢላማቸውን መትተዋል። በተጨማሪም የኢራን አብዮታዊ ዘብ በኳታር በሚገኝ የአሜሪካ ጦር ሰፈር ውስጥ ያለ የረጅም ርቀት ሚሳኤል መቃኛ ራዳር ማውደሙን አስታውቋል።
በሆርሙዝ ሰርጥ ዙሪያ ያለው የነዳጅ ጫኝ መርከቦች እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል። የኢራን አብዮታዊ ዘብ የሆርሙዝ ሰርጥ ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ እና የማንኛውም ነዳጅ ጫኝ መርከብ እንቅስቃሴ እንዲታገድ ትእዛዝ አስተላልፏል። ቆየት ብሎ ግን የኢራን ባለሥልጣናት "ወዳጅ አገሮች" በወሽመጡ በኩል እንዲያልፉ እንደሚፈቀድላቸውገልጸዋል።
የዓለም አቀፍ የነዳጅ መስመሮች ስርጭት ካርታ
በሚናብ፣ ኢራን የተከሰተው አሳዛኝ ክስተት
የአሜሪካ ቶማሃውክ ክሩዝ ሚሳኤል በኢራን ሚናብ በሚገኝ የሴቶች ትምህርት ቤት ላይ ጉዳት አደረሰ
የካቲት 28 ቀን2026 (እ.ኤ.አ) በደረሰ የሚሳኤልጥቃት የአንደኛ ደረጃ የሴቶች ትምህርት ቤት ወድሟል። ይህም ቀውሱ ከተጀመረ ወዲህ ከተመዘገቡት እጅግ ዘግናኝ ክስተቶች አንዱ ሆኗል። ሁለት የአሜሪካ "ቶማሃውክ" ክሩዝ ሚሳኤሎች ሻጃሬህ ታይቤህ (Shajareh Tayyebeh) የተሰኘውን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መትተዋል። የተለያዩምንጮች እንደሚያመለክቱት፣ እድሜያቸው ከ7 እስከ 12 የሆኑከ168 እስከ175 የሚደርሱ ተማሪዎች እና መምህራን የተገደሉ ሲሆን፣ ሌሎች በደርዘን የሚቆጠሩ ደግሞ ቆስለዋል።
በሚናብ ትምህርት ቤት ላይ የተፈጸመ ጥቃት - Sputnik አፍሪካ
በሚናብ ትምህርት ቤት ላይ የተፈጸመ ጥቃት
በሚናብ ትምህርት ቤት ላይ የተፈጸመ ጥቃት - Sputnik አፍሪካ
በሚናብ ትምህርት ቤት ላይ የተፈጸመ ጥቃት
በሚናብ ትምህርት ቤት ላይ የተፈጸመ ጥቃት - Sputnik አፍሪካ
በሚናብ ትምህርት ቤት ላይ የተፈጸመ ጥቃት
በሚናብ ትምህርት ቤት ላይ የተፈጸመ ጥቃት - Sputnik አፍሪካ
በሚናብ ትምህርት ቤት ላይ የተፈጸመ ጥቃት
1.
በሚናብ ትምህርት ቤት ላይ የተፈጸመ ጥቃት
2.
በሚናብ ትምህርት ቤት ላይ የተፈጸመ ጥቃት
3.
በሚናብ ትምህርት ቤት ላይ የተፈጸመ ጥቃት
4.
በሚናብ ትምህርት ቤት ላይ የተፈጸመ ጥቃት
168 ተማሪዎች ለህልፈት የተዳረጉበትን በሚናብ የሚገኝ ትምህርት ቤት ላይ የተሰነዘረውን የአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት የሚያሳይ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተዘጋጀ ቪዲዮ

መላምቶች እና ምርመራ፦

l ኢራን አሜሪካን እና እስራኤልን በጦር ወንጀል ከሰሰች፤ መጋቢት 6 ቀን (እ.ኤ.አ) የሰነዘረችው የአጸፋ ጥቃትም "ለሚናብ ሕፃናት የተወሰደ በቀል" እንደሆነ ገልጻለች።

l መጀመሪያ ላይ አሜሪካ እጇ እንዳለበት ብታስተባብልም፣ ትራምፕ ግን ጥቃቱ በራሱ በኢራን የተፈጸመ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመው ነበር። ሆኖም የፔንታጎን የውስጥ ምርመራ ጥቃቱ በአሜሪካ ጦር የመፈጸም ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑን አመልክቷል።

l የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ፣ አሜሪካ እና እስራኤል በደቡብ ኢራን በሚገኝ የሴቶች ትምህርት ቤት ላይ ጥቃት የፈጸሙት በስለላ ስህተት ወይም በሰውሰራሽ አስተውሎት አልጎሪዝም ብልሽት ምክንያት ተቋሙን እንደ ወታደራዊ ኢላማ በስህተት በመመደባቸው ሊሆን ይችላል።

በሚናብ ትምህርት ቤት ላይ የተፈጸመ ጥቃት
የኢራን ከፍተኛ አመራሮች መገደል መረጋገጥ
መጋቢት 1 ቀን (እ.ኤ.አ) የኢራን መንግሥታዊ መገናኛ ብዙኃን የካቲት 28 ቀን (እ.ኤ.አ) ማለዳ በመኖሪያ ቤታቸው የተገደሉትን የጠቅላይ መሪው አያቶላ አሊ ካሜኒን ሞት አረጋግጠዋል።
በካዛን በሚገኘው የኢራን ቆንስላ ጄኔራል የሀዘን አበባ የማስቀመጥ ስነ-ስርዓት - Sputnik አፍሪካ
በካዛን በሚገኘው የኢራን ቆንስላ ጄኔራል የሀዘን አበባ የማስቀመጥ ስነ-ስርዓት
የሀገሪቱ የበላይ መሪ አሊ ካሜኒ መሞታቸውን ተከትሎ በሞስኮ በሚገኘው የኢራን ኤምባሲ ደጃፍ ያለው ሁኔታ - Sputnik አፍሪካ
የሀገሪቱ የበላይ መሪ አሊ ካሜኒ መሞታቸውን ተከትሎ በሞስኮ በሚገኘው የኢራን ኤምባሲ ደጃፍ ያለው ሁኔታ
ለኢራን የቀድሞ የበላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ የተዘጋጀ የመታሰቢያ ሰልፍ - Sputnik አፍሪካ
ለኢራን የቀድሞ የበላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ የተዘጋጀ የመታሰቢያ ሰልፍ
1.
በካዛን በሚገኘው የኢራን ቆንስላ ጄኔራል የሀዘን አበባ የማስቀመጥ ስነ-ስርዓት
2.
የሀገሪቱ የበላይ መሪ አሊ ካሜኒ መሞታቸውን ተከትሎ በሞስኮ በሚገኘው የኢራን ኤምባሲ ደጃፍ ያለው ሁኔታ
3.
ለኢራን የቀድሞ የበላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ የተዘጋጀ የመታሰቢያ ሰልፍ

በአገሪቱ የ40 ቀናት የሐዘን አዋጅ ታውጇል። በአሜሪካ እና እስራኤ ልጥቃት የአያቶላው ልጅ፣ አማች፣የልጅ ልጅእና ምራትም አብረው ተገድለዋል።

የሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሞትም ተረጋግጧል፦የመከላከያ ሚኒስትር አዚዝ ናሲርዛዴህ፣ የኢራን አብዮታዊ ዘብ (IRGC) አዛዥ መሐመድ ፓክፑር፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም አብዱልረሂም ሙሳቪ እና አማካሪው አሊሻምካኒ ይገኙበታል።

አያቶላ አሊ ሬዛ አራፊ በጊዜያዊነት የአገሪቱ ጠቅላይ መሪ ሆነው ተሹመዋል።

አያቶላ አሊሬዛ አራፊ፤ የኢራን የሃይማኖት ትምህርት ቤቶች ኃላፊ፣ የጥበቃ ምክር ቤት አባል እና የባለሙያዎች ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ። - Sputnik አፍሪካ
አያቶላ አሊሬዛ አራፊ፤ የኢራን የሃይማኖት ትምህርት ቤቶች ኃላፊ፣ የጥበቃ ምክር ቤት አባል እና የባለሙያዎች ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ።
እየተስፋፋ የመጣው ግጭት

መጋቢት 2 ቀን 2026 (እ.ኤ.አ) ኢራን በእስራኤል፣ በቀጠናው በሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች እና በኢራቅ በሚገኘው የኢርቢል አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ተከታታይ ጥቃቶችን ሰንዝራለች። በዱባይ፣ ዶሃ እና ባህሬንምየፍንዳታ ድምፆች ተሰምተዋል። የኢራን አብዮታዊ ዘብ ከ700 በላይ ድሮኖችን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሚሳኤሎችን በመጠቀም60 ስልታዊ እና 500 ወታደራዊ የአሜሪካ እና የእስራኤል ተቋማት ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።

በኢራቅ የሚገኘው የእስልምና ተቃውሞ ቡድን በባግዳድ በሚገኘው "ቪክቶሪያ" ወታደራዊ ካምፕ ላይ የተሰነዘሩ የድሮን ጥቃቶችን የሚያሳይ ምስል ይፋ አደረገ
የኢራን ከፍተኛ የብሔራዊ ደህንነት ምክርቤት ጸሐፊ አሊ ላሪጃ ኒቴህራን ከአሜሪካ ጋር ምንም ዓይነት ድርድር እንደማታደርግ በይፋ ገልጸዋል።
ሄዝቦላህ የጠቅላይ መሪ አሊ ካሜኒን ግድያ ለመበቀል በሚል በእስራኤል ላይ ንቁ ወታደራዊ ጥቃት ዳግም ጀምሯል። በዚያው ዕለት እስራኤል በደቡባዊ [ሊባኖስ] ላይ፣ የቤሩትሰፈሮች እ ናየከተማዋ ዳርቻዎች ላይ ጥቃት ሰንዝራለች። በጥቃቱም የሄዝቦላህ የፓርላማ ቡድን መሪ የሆኑት መሐመድራድ ተገድለዋል።
እስራኤል በቤሩት በሚገኘው የሄዝቦላህ ተቋማት ላይ በሚሳኤል በሰነዘረችው ጥቃት 31 ሰዎች ሲገደሉ 140 ደግሞ ቆስለዋል።
የስፑትኒክ ዘጋቢ በቴህራን በዘገባ ላይ
የአሜሪካ አየር ኃይል ንብረት የሆነች F-15 ተዋጊ ጄት በኩዌት ሰማይ ላይ ተከስክሳለች። የኢራን መገናኛ ብዙኃን ጄቷ በኢራን ሚሳኤል እንደ ተመታች ቢገልጹም፣ አሜሪካ ግን በአጋጣሚ በራሷ ኃይሎች እንደ ተመታች ተናግራለች።
የኢራን ጥቃቶች በቀጠናው እና የላቁ የጦር መሣሪያዎች አጠቃቀም

• ከመጋቢት 3 እስከ መጋቢት 10 ቀን (እ.ኤ.አ) ባለው ጊዜ ውስጥ የኢራን አብዮታዊ ዘብ (IRGC) በባህሬን የሚገኘውን የአሜሪካ አየር ኃይል ጣቢያ በሚሳኤል እና በድሮን ደብድቧል። በተጨማሪም በእስራኤል የሚገኙ ኢላማዎችን፦ በቂሳሪያ የሚገኘውን የጦር ሰፈር፣ በብኒብራክ፣ ፔታህቲክቫ፣ ምዕራባዊ ጋሊሊ፣ ቤንጉሪዮን አውሮፕላን ማረፊያ እና በቴልአቪቭ የሚገኘውን የመከላከያ ሚኒስቴር መትቷል።

• የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጥቃቱን ወደ አዲስ ምዕራፍ ማሸጋገሩን እና ስልታዊ እንዲሁም ድምፅን ከአምስት እጥፍ በላይ የሚቀድሙ (ሃይፐርሶኒክ ) ሚሳኤሎችን (ጋድር፣ ኢማድ፣ፋታህ እናኬይባር ሸካን) እየተጠቀመ መሆኑን አስታውቋል። የአየር እና የጠፈር ኃይሎች ዕዝ ከእንግዲህ በኋላ የሚሳኤሎቹ አረር ቢያንስ አንድቶን እንደሚመዝን ገልጸዋል። ኢራን በእስራኤል ላይ እጅግ ዘመናዊ የሆነውን "ኮራምሻህር-4" (2,000 ኪ.ሜየሚጓዝ እና 1,500 ኪ.ግ አረር መሸከም የሚችል) ሚሳኤል ተጠቅማለች።

• ኢራን 22ኛውን የ"ኮራምሻህር-4" እና የ"ፋታህ" ሚሳኤል ጥቃት ማዕበል ሰንዝራለች። አብዮታዊ ዘቡ በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እና በጆርዳን የሚገኙየ"ታድ" (THAAD) ሚሳኤል መከላከያ ራዳሮችን፣ እንዲሁም በኳታር የሚገኘውን "ኤፍፒኤስ132" የተሰኘ ራዳርማውደሙን ይፋ አድርጓል።

ግንቦት 25 ቀን 2023 (እ.ኤ.አ) የኢራን መከላከያ ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው በዚህ ምስል፤ ኮራምሻህር-4 የተሰኘ ሚሳኤል ስሙ ባልተጠቀሰ ስፍራ ሲተኮስ (በኢራን መከላከያ ሚኒስቴር በኩል ለኤፒ የቀረበ)  - Sputnik አፍሪካ
ግንቦት 25 ቀን 2023 (እ.ኤ.አ) የኢራን መከላከያ ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው በዚህ ምስል፤ ኮራምሻህር-4 የተሰኘ ሚሳኤል ስሙ ባልተጠቀሰ ስፍራ ሲተኮስ (በኢራን መከላከያ ሚኒስቴር በኩል ለኤፒ የቀረበ)

የኢራኑ ፕሬዝዳንት በበኩላቸው ጎረቤት አገራት ከግዛታቸው የሚነሱ ጥቃቶች ከሌሉ ወይም በኢራን ላይ እንዲፈጸም ካልፈቀዱ፣ ኢራንም በእነርሱ ላይ የምታደርገውን ጥቃት እንደምታቆም ገልጸዋል።

የኢራን የስትራቴጂ ለውጥ
መጋቢት 11 ቀን 2026 (እ.ኤ.አ) የኢራን ጦር ኃይሎች ከእስራኤል እና ከአሜሪካ ጋር ለሚያደርጉትጦርነት አዲስ ስትራቴጂ እና የሚጠቀሙባቸውን የታክቲክ መርሆች እንደቀየሩ አስታውቀዋል። በዚህም መሠረት በባሕረ ሰላጤው አገራት ውስጥ ከወራሪዎች ጋር ግንኙነት ባላቸው ተቋማት ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት ቀጣይነት ያለው እንደሚሆንና አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የሚፈጽሙትን ጥቃት ጠብቆ የሚሰነዘሩ (የአጸፋ እርምጃ) እንደማይሆኑ ገልጻለች።
ሒዝቦላ በእስራኤል ላይ "ኢትንሊቭስ" የተሰኘ በጥሬ ትርጉሙ "የተበሉ ቅጠሎች" ያለውን አዲስ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሩን አስታውቆ፣ ከሊባኖስ ወደ ሰሜን እስራኤል 100 ሮኬቶችን ተኩሷል። ሄዝቦላህ እና ኢራን ይህንን"የመጀመሪያው የተቀናጀጥቃት" ሲሉ ጠርተውታል። ኢራን ከሊባኖሱ ሄዝቦላህ ጋር በመተባበር በእስራኤል ውስጥ ከ50 በላይ ኢላማዎችን መትታለች።

l ኢራን ከአሜሪካ ጋር ለሚደረግና ከ10 ዓመታት በላይ ለሚዘልቅ ጦርነት ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች፦ "ከእንግዲህ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ሊታሰብ የማይችል ጉዳይ ነው" ብላለች።

አሜሪካ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን እና የጦር መሣሪያዎችን እየተጠቀመች ነው
  • የዚህ ወታደራዊ ዘመቻ ተለይቶ የሚታወቅ ባህሪ ሰው ሰራሽ አስተውሎት በከፍተኛ ሁኔታ ጥቅም ላይ መዋሉ ነው። እንደ የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) ቃል አቀባይ ገለጻ፣ የሰው ልጅ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ነጥቦችን ለይቶ እንዲያወጣ መረጃዎችን በቅድሚያ የማቀናበሩ ሥራ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት ተሰጥቷል።ሆኖም የጥቃት ኢላማ የመምረጥ እና የመተኮስ ውሳኔ የሚወሰነው በሰዎች ነው።
  • የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ትክክለኛ ኢላማን የሚመቱ ሚሳይሎችበምህጻረቃሉ ( ፒአራኤስኤም) የተሰኙ ሚሳኤሎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ ማዋሉን አረጋግጧል። ይህ ሚሳኤል የጦር ሠራዊት ታክቲካዊ የሚሳይል ሥርዓት ወይም በምህጻረ ቃሉ የ"ኤቲኤሲኤምሲ" ባለስቲክ ሚሳኤል ውጤት ሲሆን፣ ከቀድሞው ሞዴል በ200 ኪ.ሜ በበለጠ ርቀት የመጓዝ አቅም አለው። እስከ 500 ኪ.ሜ የሚወነጨፍ ሲሆን ተንቀሳቃሽ ከሆነው ከፍተኛ የመንቀሳቀስ ብቃት ያለው የመድፍ ሮኬት ሥርዓት በምህጻረቃሉ የ"ኤች አይ ኤም አር ኤስ" ተንቀሳቃሽ ማስወንጨፊያ ላይ ይተኮሳል።
  • ሌላው አዲስ የታ የመሣሪያ የሌዘር ቁጥጥርና ትንተና ሥርዓት (ሉካስ) የተሰኘው "ካሚካዜ" (ራስን አጥፊ) ድሮን ነው። ይህ ድሮን የታወቀው የኢራን "ሻሄድ" ድሮን ቅጂ ሲሆን፣ እንደ ሚዲያ ዘገባዎች ከሆነ የአንዱ ዋጋ 35,000 ዶላር ነው።
በጦርነቱ ምክንያት የተፈጠረው የዓለም ማህበረሰብ መከፋፈል
በኢራን ላይ የተከፈተው ወታደራዊ ዘመቻ በዓለም ማህበረሰብ መካከል ያለውን የጎራ መለየት ይበልጥ አባብሶታል። የኢራን አጋር የሆኑት ሩሲያ እና ቻይና ጥቃቱን ሲያወግዙ፣ የአሜሪካ የምዕራባውያን እና የቀጠናው አጋሮች ግን ለጥቃቱ መከሰት ቴህራንን ተጠያቂ አድርገዋል።
የሩሲያ ምላሽ ፈጣን ነበር ፦ ፕሬዝዳንትፑቲን መጋቢት 1 ቀን (እ.ኤ.አ) ለኢራኑ ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዘሽኪያን በጠቅላይ መሪው አያቶላ አሊ ካሜኒ እና በቤተሰባቸው ግድያ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል። ግድያውም ሁሉንም የሰብአዊ ሞራል እና አለም አቀፍ ህግጋትን በንቀት በመጣስ እንደተፈጸመ ጠቁመዋል። ፑቲን በተጨማሪም ግጭቶችን በአስቸኳይ ማቆም፣ በኢራን ዙሪያ እና በመካከለኛው ምስራቅ በሙሉ ችግሮችን ለመፍታት የኃይል ዘዴዎችን መተው፣ እንዲሁም ወደ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ መንገድ በፍጥነት መመለስ እንደሚያስፈልግ የሩሲያን መርህ የጠበቀ አቋም በድጋሚ አረጋግጠዋል።
ጀርመን፣ ፈረንሳይ እና ብሪታንያ በኢራን ላይ በተፈጸመው ጥቃት ተሳትፎ እንደሌላቸው ቢገልጹም፣ ኢራን የሰነዘረችውን ጥቃት ግን አውግዘዋል።
ጣሊያን እናስፔን፦ ሁኔታውን በተረጋጋ ሁኔታ መመልከትን መርጠዋል።
የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ሳንቼዝ፦ዶናልድ ትራምፕ ስፔን በኢራን ላይ ጥቃት ለመሰንዘር የጦር ሰፈሮቿን ባለመፍቀዷ ቅሬታቸውን ቢገልጹም፣ የሳንቼዝ መንግሥት ግን "ለጦርነትን አያስፈልግም " የሚል አቋም ይዟል።
የሰፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የፈጸሙትን ወረራ አስመለክቶ መግለጫ ሲሰጡ፤ መጋቢት 4 ፣ 2026 (እ.ኤ.አ)

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ሜሎኒ፦ በሮም ለፓርላማ ባደረጉት ንግግር አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የፈጸሙትን ጥቃት አውግዘዋል። በመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ ዘመቻ "ከዓለም አቀፍ ሕግ ውጭ የሆኑ የአንድ ወገን ጣልቃ ገብነቶች" አካል መሆኑን ገልጸዋል።

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜሎኒ ፦ መጋቢት 2 ቀን 2018 ዓ.ም በሮም ፓርላማ ባደረጉት ንግግር አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የሰነዘሩትን ጥቃት አወገዙ
በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል የሚደረገው የትራንስፖርት መቀነስ እና የነዳጅ ቀውስ
በኢራን ላይ የተሰነዘረውን የአሜሪካ እና የእስራኤል ጥቃት ተከትሎ፣ በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል የሚደረገውየመርከብ ጉዞ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። የኢንሹራንስኩ ባንያዎችም እየታየ ባለው የደህንነት ስጋት ምክንያት የወታደራዊ ክፍያዎችን ማሳደግ እና የኢንሹራንስ ሽፋን ውላቸውን መከለስ ጀምረዋል። ምንም እንኳን ይፋዊ የሆነ የእንቅስቃሴ እገዳ ባይኖርም፣ በጸጥታ ስጋት ምክንያት ገበያው በማጓጓዝ ረገድ በተጨባጭ የሚታይ የመቀዝቀዝ (መቆም) ሁኔታ ገጥሞታል።
የሆርሙዝ ሰርጥ ስልታዊ ጠቀሜታ ያለው መተላለፊያ ነው፣ ይህ ሰርጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ 30% የሚሆነውን ፈሳሽየ ተፈጥሮ ጋዝ እና ወደ 20% የሚጠጋውን የነዳጅ እና የነዳጅ ውጤቶች ዝውውር የሚያስተናግድ ወሳኝ መተላለፊያ ነው። እየጨመረ በመጣው ስጋት ምክንያት በጀርመን፣ ጃፓን፣ፈረንሳይ እና ሌሎች አገራት የሚገኙ ግዙፍ የመርከብ ኩባንያዎች በዚህ መስመር የሚያደርጉትን ጉዞ አቁመዋል።

ኢራን በይፋ በሰጠችው መግለጫ በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ ያላትን የባህር ላይ ሉዓላዊነት እንደምታስከብር ገልጻለች። ኢራን የሚያልፉ መርከቦችን በዓለም አቀፍ ፕሮቶኮል መሠረት እንደምታስተናግድ ብትገልጽም፣ "ለወታደራዊ ዓላማ በሌሎች አገራት የሚያገለግሉ" የንግድ መርከቦችን ግን ለይታ እንደምታውቅና "እንዲንቀሳቀሱ እንደማትፈቅድ" አስታውቃለች።

ኢራን ቆየት ብላ ባወጣችው መግለጫ፣ ማንኛውም የአረብ ወይም የአውሮፓ አገር የእስራኤልን እና የአሜሪካን አምባሳደሮች ከግዛቱ ካስወጣ፣ በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል በነፃነት የመንቀሳቀስ መብት እንደሚሰጠው ገልጻለች።

እስከ መጋቢት 18 ቀን 2026 (እ.ኤ.አ) የደረሰው የጉዳት መጠን ማጠቃለያ
በኢራን ላይ በተካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ የደረሰ የሰው ህይወት ጉዳት። - Sputnik አፍሪካ
በኢራን ላይ በተካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ የደረሰ የሰው ህይወት ጉዳት።

• እስከ መጋቢት18 ቀን 2026 (እ.ኤ.አ)ድረስ በነበረው ግጭት ከፍተኛ የሰው ሕይወት መጥፋት እና ሰፊ ሰብአዊ ቀውስ ተከስቷል።

• እንደ ኢራን መንግሥት ይፋዊመረጃ ቢያንስ 1,348 ሲቪሎች ሲገደሉ፣ከ17,000 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል።

• በጎረቤት አገራት፦ግጭቱ ጎረቤት አገራትንም ነክቷል። በእስራኤል አራት ሕፃናትን ጨምሮ 12 ሰዎች ተገድለዋል። በሊባኖስ 98 ሕፃናት እና 52 ሴቶችን ጨምሮ ቢያንስ 687 ሰዎች እና ሦስት ወታደሮች ተገድለዋል። በባሕረ ሰላጤዉ አገራት ሰባት የአሜሪካ ወታደሮችን ጨምሮ 24 ሰዎች ሲገደሉ፣ በኢራቅ ደግሞ 31 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

• በቀጠናው በቀጥታ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ2,000 በላይ ሆኗል። ሆኖም በኢራን ውስጥ ያለው ሰብአዊ ቀውስ እጅግ የከፋ ነው፤ እንደ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን መረጃ ከሆነ፣ እስከ3.2 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው ለአገርውስጥ ስደት ተጋልጠዋል።

በከፍተኛ አመራሩ ላይ የደረሰ ድንገተኛ ጥቃት፦ የላሪጃኒ ሞት የኃይል ሚዛኑን የማይለውጠው ለምንድን ነው?

የኢራን ከፍተኛ የብሔራዊ ደህንነትምክር ቤት ጸሐፊ አሊ ላሪጃኒ መገደል (መጋቢት 17 ቀን ፣ እ.ኤ.አ) በአገሪቱ አመራር ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደማያደርስ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ አስታውቀዋል።

ጥቅምት 22 ቀን 2015 (እ.ኤ.አ) የኢራን የኢስላማዊ አማካሪ ምክር ቤት (ፓርላማ) አፈ ጉባኤ አሊ ላሪጃኒ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በ12ኛው የቫልዳይ ዓመታዊ የውይይት መድረክ ላይ ሲገናኙ። - Sputnik አፍሪካ
ጥቅምት 22 ቀን 2015 (እ.ኤ.አ) የኢራን የኢስላማዊ አማካሪ ምክር ቤት (ፓርላማ) አፈ ጉባኤ አሊ ላሪጃኒ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በ12ኛው የቫልዳይ ዓመታዊ የውይይት መድረክ ላይ ሲገናኙ።

"አሜሪካውያን እና እስራኤላውያን ይህንን እስካሁን ለምን እንዳልተረዱ አላውቅም፤ የኢራን ኢስላማዊ ሪፐብሊክ የጸና የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ተቋማት መዋቅር ያላት አገር ናት" ብለዋል። አራግቺ አክለውም የካቲት 28 (እ.ኤ.አ) ቀን የጠቅላይ መሪው አሊ ካሜኒ ግድያ ከተፈጸመ በኋላም የመንግሥት ሥርዓቱ ሳይናወጥ ሥራውን መቀጠሉን አስታውሰዋል።

የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የላሪጃኒን ግድያ "የሽብር ጥቃት" ሲል የጠራው ሲሆን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክርቤት ተጠያቂዎቹን ለፍርድ እንዲያቀርብ ጠይቋል።
በኢራን ግጭት ምክንያት የደረሱ የኢኮኖሚ ኪሳራዎች
የአሜሪካ የጦርነት ወጪ
የመጀመሪያው የጦርነት ሳምንት ብቻ የአሜሪካ በጀት ቢያንስ 11.3 ቢሊዮን ዶላር ወጪ አስከትሏል። ይህ ወጪ በዋነኝነት ለጦር መሣሪያዎች የዋለ ሲሆን፣ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት ብቻ ፔንታጎን ለላቁ የሚሳኤል መሣሪያዎች 5.6 ቢሊዮን ዶላር አውጥቷል (ለምሳሌ፦አንድ የኤጂኤም-154 ቦምብ ብቻ እስከ 836,000 ዶላር ያወጣል)። በአሁኑ ወቅት አሜሪካ ለኢራኑ ጦርነት በቀን በአማካይ 1 ቢሊዮን ዶላር እየገበረች ትገኛለች።
የትራምፕ አስተዳደር ተጨማሪ 50 ቢሊዮን ዶላር ከኮንግረ ስለመጠየቅ ዝግጅት እያደረገ ቢሆንም፣ በኮንግረሱ ውስጥ ግን መከፋፈል ይታያል፦ ዴሞክራቶች ግልጽ የሆነ የጦርነት ስትራቴጂ እንዲቀመጥ ሲጠይቁ፣ የተወሰኑ ሪፐብሊካኖች ደግሞ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ወጪ እንዳይኖር ስጋታቸውን ገልጸዋል። በአስተዳደሩ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ወገኖች ደግሞ 50 ቢሊዮን ዶላር እንኳ ቢሆን ከሚፈለገው በታች እንደሆነ ያምናሉ።
የነዳጅ ገበያ

መጋቢት 12 ቀን (እ.ኤ.አ) በለንደን የንግድ ልውውጥ የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ከ100 ዶላር በላይ ሆኗል። ይህም ከ2024 ክረምት ወዲህ የተመዘገ በከፍተኛው ዋጋ ነው። ለዚህም ምክንያት የሆነው በባሕረ ሰላጤው ሀገራት ውስጥ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ሲሆን፣ በኢራቅ ጠረፍ አቅራቢያ በነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ የተፈጸመው ጥቃት የኢራቅ ወደቦች ለጊዜው እንዲዘጉና በኦማን የሚገኝ የነዳጅ ማከማቻ እንዲለቀቅ አድርጓል።

ገበያው በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል ካለው የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል ስጋት የተነሳ ከፍተኛ መዋዠቅ እያሳየ ይገኛል።

የዓለም የነዳጅ ክምችት እስከ መቼ ይቆያል?
የወርቅ ዋጋ መናር
በጂኦፖለቲካዊ አለመረጋጋት ምክንያት ባለሀብቶች ሀብታቸውን ወደ አስተማማኝ ንብረቶች እያዛወሩ ነው። በዚህም ምክንያት ወርቅ በታሪኩ ከፍተኛው ዋጋ ላይ በመድረስ አንድ አውንስ ወርቅ 5,213 ዶላር (ከባለፈውዓመት የ77% ጭማሪ) ደርሷል። የገንዘብ መጠን (88.59 ዶላር) እና ፕላቲኒየም (2,202 ዶላር) በተመሳሳይ ዋጋቸው ጨምሯል። የፊች ሬቲንግስ የማዕከላዊ ባንኮች እና የባለሀብቶችን ከፍተኛ ግዢ መሠረት በማድረግ፣ የ2026 የወርቅ ዋጋ ግምት ወደ 4,500 ዶላር ከፍ እንዲል አድርጓል።
የአሜሪካ የጦርነት ወጪ
Go back to the beginningGo back to the main page
15:56 20.03.2026 (የተሻሻለ: 13:24 03.04.2026)
አዳዲስ ዜናዎች
0