"የአሜሪካ መራሹ የዓለም ሥርዓት እያከተመ ነው" – ከፍተኛ ተመራማሪ
20:42 19.03.2026 (የተሻሻለ: 20:44 19.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"የአሜሪካ መራሹ የዓለም ሥርዓት እያከተመ ነው" – ከፍተኛ ተመራማሪ
"ሚሳኤሎች ከሰማይ እየዘነቡ" ስንመለከ፣ ነባሩ የዓለም ሥርዓት እየተቀየረ እንደሆነ አመላካች መሆኑን በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ (ዩኒሳ) የልማት ጥናቶች ከፍተኛ መምህርና ተመራማሪው ዶክተር ለሃሳ ሞሎይ ለስፑቲኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
“እነዚህ ክስተቶች እየተለወጠ ያለውን ዓለም አቀፋዊ ሥርዓት አመላካች ናቸው፡፡ በተለይም ‘የሞት ሥልጣኔ’ ተብሎ የሚጠቀሰው ሥልጣኔ ማክተሚያ ምልክቶች ናቸው። ይህም ሌሎችን ያላካተተ ነገር ግን በሌሎች ትከሻ ላይ የተገነባው ‘የአሜሪካ የዓለም ፕሮጀክት’ ሥርዓት የማብቂያው ምዕራፍ መሆኑን ያሳያል።” ብለዋል፡፡
ዶክተር ሞሎይ፣ የወደፊቱ የዓለም ሥርዓት የሰው ልጅ ሕይወት የሚከበርበት፣ በጋራ አብሮ መኖር የሚያስችልና ባለብዙ-ዋልታ እንደሚሆን አስረድተዋል። የለውጥ አስፈላጊነትንም አጉልተዋል፡፡
ጦረኛ በሆነ የአንድ ወገን የበላይነትና በኃይል ላይ የተመሠረተው የቅኝ ግዛት ሞዴል ሊያበቃ እንደሚገባም አሳስበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X