በሱማሊያ፣ ፌዴራል መንግሥት እና የደቡብ ምዕራብ ግዛት ኃይሎችን እያሰባሰቡ መሆኑን ተከትሎ የፖለቲካ ውጥረት ነግሷል

ሰብስክራይብ

በሱማሊያ፣ ፌዴራል መንግሥት እና የደቡብ ምዕራብ ግዛት ኃይሎችን እያሰባሰቡ መሆኑን ተከትሎ የፖለቲካ ውጥረት ነግሷል

​የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት በመቶዎች የሚቆጠሩ የኤሊት ፖሊስ አባላትን የአየር ትራንስፖርት በመጠቀም ከመቃዲሾ ወደ ደቡብ ምዕራብ ግዛት የአስተዳደር ማዕከል ወደሆነችው ባራዌ መላኩን የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን በዛሬው ዕለት ዘግበዋል።

​የዚህ እንቅስቃሴ ዓላማ የፌዴራል መንግስቱን ቁጥጥር፣ ከባራዌ የተነሱ የሀገር ውስጥ ተቃዋሚ ሚሊሻዎች በቅርቡ ወደ ተሰባሰቡበትና በባይ ክልል ወደሚገኘው የቡርሃካባ ወረዳ ለማስፋፋት እንደሆነ ተገልጿል።

ሁኔታውን ተከትሎ የወጡ ቁልፍ መረጃዎች፦

▪ የደቡብ ምዕራብ ግዛት ማክሰኞ ዕለት ከሞቃዲሾ ጋር ያለውን ግንኙነት በሙሉ አቋርጧል። የግዛቱ አስተዳደር የፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ መንግሥት፣ ፕሬዝዳንት አብዲአዚዝ ላፍታጋሪንን ከስልጣን ለማውረድ እና ክልሉን ለማተራመስ ታጣቂዎችን እያስታጠቀ ነው ሲል ከሷል፤ የፌዴራል ባለስልጣናት በበኩላቸው ክሱን ውድቅ አድርገዋል።

▪ የፌዴራል መንግሥት የትብብር መቋረጡን የኮነነ ሲሆን፣ ብሔራዊ አንድነትን ለመጠበቅ ውይይት እና እርቅ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

▪ ማክሰኞ ዕለት የግዛቱ ፕሬዝዳንት ላፍታጋሪን ሶማሊያን ከሚያስተዳድረው የፍትህ እና አንድነት  ፓርቲ መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።

▪ ከረቡዕ ጀምሮ ግዛቱ ወደ አየር ማረፊያዎቹ የሚደረጉ ማናቸውንም የንግድ እና የግል በረራዎች ያገደ ሲሆን፣ የተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪካ ሕብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ በሶማሊያ በረራዎች ብቻ እንዲፈቀዱ መወሰኑን የደቡብ ምዕራብ ትራንስፖርት ሚኒስቴርን ጠቅሰው የሶማሊያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

▪ የቀድሞው የሱማሊያ ፕሬዝዳንት ፋርማጆ የወቅቱ ፕሬዚዳንት መሀሙድ የስልጣን ዘመን ግንቦት 23 የሚያበቃ ቢሆንም፣ "የፖለቲካ እና የሕገ-መንግሥታዊ ክፍተትን ለመከላከል ሰፊ ስምምነት እና የፖለቲካ ውሳኔ ያስፈልጋቸዋል" ብለዋል።

▪ ውጥረቱ የመነጨው በመጋቢት ወር አጋማሽ ላይ በፀደቀው የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ነው (ይህም የፕሬዝዳንቱን እና የፓርላማውን የስልጣን ዘመን ከ4 ወደ 5 ዓመት ከፍ የሚያደርግ፣ የፓርላማ አባላት በቀጥታ በዜጎች እንዲመረጡ የሚያደርግ እና ተጨማሪ ስልጣንን ለፌዴራል መንግሥቱ የሚሰጥ ነው)፤ ይህ ማሻሻያ በደቡብ ምዕራብ ግዛት ውድቅ ተደርጓል።

ቪዲዮው የደቡብ ምዕራብ ግዛት አስተዳደር ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋር ያለውን ትብብር በሙሉ ማቋረጡን የሚገልጽ ይፋዊ መግለጫ ሲሰጥ ያሳያል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0