የአፍሪካ ሕብረት በመካከለኛው ምስራቅ ካለው ቀውስ አንጻር የአፍሪካን የፋይናንስ መከላከያ መገንባት አለበት- የአፍሪካ ኢነርጂ ምክር ቤት

የአፍሪካ ሕብረት በመካከለኛው ምስራቅ
የአፍሪካ ሕብረት በመካከለኛው ምስራቅ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.03.2026
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሕብረት በመካከለኛው ምስራቅ ካለው ቀውስ አንጻር የአፍሪካን የፋይናንስ መከላከያ መገንባት አለበት- የአፍሪካ ኢነርጂ ምክር ቤት

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት የዋጋ ግሽበትን በመጨመር እና አፍሪካ በየዓመቱ ለምትከፍለው 89 ቢሊዮን ዶላር የዕዳ ወለድ ላይ ጫና እየፈጠረ ባለበት በዚህ ወቅት፤ የአፍሪካ ሕብረት በዕዳ ላይ ከተመሰረተ የፋይናንስ ስርዓት ወጥቶ በአፍሪካ- መራሽ የፋይናንስ አማራጮች ላይ ማተኮር እንዳለበት የአፍሪካ ኢነርጂ ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ ኤንጄ አዩክ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

እንደ ዋና ሰብሳቢው ገለጻ፣ ቀዳሚ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፦

የሀገራትን የበጀት አቅም ለመጠበቅ ቀጣናዊ የፋይናንስ ምንጮችን ማሰባሰብ፣

ድንበር ተሻጋሪ የካፒታል ፍሰትን ለማሳለጥ ውጤታማ ያልሆኑ የውጭ ምንዛሬ ደንቦችን እና ቢሮክራሲያዊ እንቅፋቶችን ማስወገድ እና

እንደ አፍሪካ ኢነርጂ ባንክ ያሉ አማራጭ የገንዘብ ምንጮችን ማሳደግ።


"አፍሪካ ያለባትን የፋይናንስ ክፍተት ለመቀነስ የሚያስችሉ አሰራሮች ቀድሞውኑ አሏት፤ ሀገራት አሰራሮቹን መጠቀም ብቻ ነው የሚጠበቅባቸው። የአፍሪካ ኢነርጂ ባንክ ቀጣናዊ ካፒታል ያቀርባል። የልማት ፋይናንስ ተቋማት የኢንቨስትመንት አቅማቸውን እያሳደጉ ነው። የጡረታ ፈንዶች እና ባንኮችም አዳዲስ የኢንቨስትመንት እድሎችን በመፈለግ ላይ ናቸው። አፍሪካ ቀጣናዊ ፋይናንስን መጠቀም መጀመር አለባት" ሲሉ ባለስልጣኑ ገልጸዋል።


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0