ሩሲያና ኢትዮጵያ ጤናን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማስፋፋት እየመከሩ ነው፦ የሩሲያ ጤና ሚኒስትር

ሩሲያና ኢትዮጵያ ጤናን ጨምሮ
 ሩሲያና ኢትዮጵያ ጤናን ጨምሮ  - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.03.2026
ሰብስክራይብ
ሩሲያና ኢትዮጵያ ጤናን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማስፋፋት እየመከሩ ነው፦ የሩሲያ ጤና ሚኒስትር


​"በሩሲያ የሕክምና ውጤቶች፣ የሕክምና መሣሪያዎች፣ መድኃኒቶች እና የኒውክሌር ሕክምና ቴክኖሎጂዎች ላይ ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን አስተውለናል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ አኅጉር ለእኛ ጠቃሚ አጋር ናት፤ ስለሆነም የሁለትዮሽ ግንኙነታችን አንዱ ቁልፍ አቅጣጫ የሩሲያ የሕክምና አምራቾች ወደ አገሪቱ ገበያ እንዲገቡ መደገፍ ሲሆን፣ በዚህ ላይም በንቃት እየሠራን እንገኛለን" ሲሉ ሚካይል ሙራሽኮከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች፣ ከምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን እና ከሌሎች በርካታ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ጋር ተገናኝተው በተወያዩበት የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ወቅት ተናግረዋል፡፡


ሁለቱ ​ወገኖቹ በአዲስ አበባ የሚገኘውንና በደጃዝማች ባልቻ ስም የሚጠራውን የሩሲያ ቀይ መስቀል ሆስፒታል፣ በአፍሪካ የመጀመሪያው የሩሲያ ባለብዙ-ዘርፍ የሕክምና ተቋም ለማድረግ ስላለው ዕቅድ መወያየታቸውን የሚኒስትሩ አማካሪ አሌክሲ ኩዝኔትሶቭ አብራርተዋል።

​በተጨማሪም በሕክምና ትምህርት ዘርፍ ያለውን ትብብር እያደገ መሆኑንና እስካሁን ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያን የጤና ባለሙያዎች በሩሲያ ሥልጠና ማግኘታቸውን አማካሪው አክለው ገልጸዋል።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0