ሩዋንዳ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውጥረትን ለማርገብ ተስማሙ - የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ሩዋንዳ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውጥረትን ለማርገብ ተስማሙ
ሩዋንዳ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውጥረትን ለማርገብ ተስማሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.03.2026
ሰብስክራይብ
ሩዋንዳ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውጥረትን ለማርገብ ተስማሙ - የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና የሩዋንዳ ተወካዮች በዋሽንግተን ተገናኝተው በምስራቅ ኮንጎ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በሚያስችሉ ተጨባጭ እርምጃዎች ላይ መወያየታቸውን ሚኒስቴሩ ባወጣው የጋራ መግለጫ አስታውቋል፡፡

ከተስማሙባቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፦

የየአገራቱን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ለማክበር ቃል መግባት፣

ሩዋንዳ በተወሰኑ የኮንጎ ግዛቶች ውስጥ ያሰፈረቻቸውን ኃይሎች በታቀደ የጊዜ ሰሌዳ ማስወጣት እና የመከላከያ እርምጃዎችን ማንሳት፣

የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ "የሩዋንዳ ነፃ አውጪ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎችን" ለማጥፋት በጊዜ የተገደበ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ እና

ለሁሉም ንጹሐን ዜጎች ጥበቃ ለማድረግ ቁርጠኝነት ማሳየት።

​ ሩዋንዳ የኤም 23 አማጺ ቡድንን እንደምትደግፍ ብትክድም፣ ኮንጎ ግን ሩዋንዳ ሉዓላዊነቴን ጥሳለች ስትል ትከሳለች። በሌላ በኩል ሩዋንዳ የኮንጎ መንግሥት ከጎርጎሮሳውያኑ 1994ቱ የኪጋሊ የዘር ማጥፋት ወንጀል ጋር ግንኙነት ያለውን የኤፍዲኤልአር ቡድንን ይረዳል ስትል ትከሳለች። ባለፈው ታኅሣሥ ወር የተፈረመው የሰላም ስምምነት ኤም 23 ኡቪራ የተባለችውን ከተማ ከተቆጣጠረ በኋላ የፈረሰ ሲሆን፣ ይህም ቀውሱ ወደ ቀጣናዊ ጦርነት ሊያመራ ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሮ ነበር።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0