የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአራት ክልሎች ውስጥ የመጠጥ ውሃ ተደራሽነት የሚያሰፋ የ400 ሚሊዮን ብር ስምምነት ፈረመ

ሰብስክራይብ

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአራት ክልሎች ውስጥ የመጠጥ ውሃ ተደራሽነት የሚያሰፋ የ400 ሚሊዮን ብር ስምምነት ፈረመ

ከስምንት ድርጅቶች ጋር የተፈረመው የውል ስምምነት በአማራ፣ በኦሮሚያ በትግራይ እና ጋምቤላ ክልሎች የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ፣ ጥናት፣ ዲዛይን እና ኤሌክትሮ መካናኒክ እቃዎች አቅርቦት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው፡፡

ፕሮጀክቱ የሚተገበርባቸው ቦታዎች፦

በአማራ ክልል – መካነ ሰላም፣ሰቆጣ እና ገለሱት፣

በኦሮሚያ ክልል – ምእራብ ሸዋ ጀዱ ወረዳ፣

በትግራይ ክልል – ማይጸብሪ እና

በጋምቤላ ክልል ድርቅ የሚያጠቃቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡

የግንባታ ፕሮከጅቶቹ በ6 ወር የጊዜ ገደብ፣ የእቃ አቅርቦት የአንድ ወር እና ጉድጓድ ቁፋሮ በ3 ወር የጊዜ ገደብ ተጠናቀው ለአገልግሎት እንደሚበቁ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0