ከሊቢያ እስከ ኢራን፦ እየተዳከመ ያለው ምዕራባዊው ዓለም በተፈጥሮ ሀብት የበለፀጉ አገራትን "ዳግም ቅኝ ለመግዛት" እየጣረ ነው- ምሁር

ሰብስክራይብ

ከሊቢያ እስከ ኢራን፦ እየተዳከመ ያለው ምዕራባዊው ዓለም በተፈጥሮ ሀብት የበለፀጉ አገራትን "ዳግም ቅኝ ለመግዛት"  እየጣረ ነው- ምሁር

​አሜሪካ የራሳቸውን ፖለቲካዊ መስመር መከተል የሚችሉና የተፈጥሮ ሃብት ያላቸውን አገራት አውድማለች፤ ለዚህም ሊቢያ ግልጽ ማሳያ ናት ሲሉ በጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ፕሮፌሰር  አሌክሲ ሃቢያሬምዬ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

"አሜሪካ እውነተኛ ዲሞክራሲን ለማስፈን ፍላጎት ኖሯት አያውቅም። እ.ኤ.አ. በ1953 በኢራኑ መሀመድ ሞሳዴግ ላይ የተካሄደው የሲአይኤ መፈንቅለ መንግስት፣ በእ.እ.አ. በ1961 የፓትሪስ ሉሙምባ ግድያ እና በሳልቫዶር አሌንዴ ላይ የተካሄደው መፈንቅለ መንግስት አሜሪካ በዲሞክራሲያዊ መንግስታት ላይ የምታደርገው ቀጥተኛ ጥቃት ማሳያዎች ናቸው" ሲሉ ሃቢያሬም አስረድተዋል።

​የአሜሪካ ዓለም አቀፋዊ ተጽዕኖ በግልጽ እየቀነሰ ቢመጣም፣ ያለ ግብግብ በቀላሉ እጃቸውን እንደማይሰጡ ምሁሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።

"የአሜሪካ ጦርም ሆነ የምዕራባውያን አጋሮቻቸው፣ የበላይነታቸውን ለተጨማሪ ጥቂት አስርት ዓመታት ለማራዘም ካላቸው ዓላማ ጋር አይሰለፉም ብለው በሚገምቷቸው አገራት ላይ ግልጽና ጨካኝ እርምጃዎችን መውሰዳቸውን ይቀጥላሉ" ሲሉ ምሁሩ ያስጠነቅቃሉ።

​እንደ እርሳቸው ገለጻ፣ የደቡባዊ ዓለም ሀገራት ይህንን ‘የዳግም ቅኝ አገዛዝ’ ሙከራ ለማክሸፍ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆን አለባቸው። አገራቱ በጋራ ከቆሙ የተሻለ የመከላከል ዕድል ይኖራቸዋል።

"የማርኮ ሩቢዮ የሙኒክ ንግግር ምልክት ከሆነ፣ አፍሪካንና ላቲን አሜሪካን መልሶ በቅኝ ለመግዛት ወደኋላ አይሉም። አሁን የቬንዙዌላን ነዳጅ እየተቆጣጠሩ ነው፣ ኩባንም ለማጥፋት እየተዘጋጁ ይገኛሉ" ሲሉ ሃቢያሬምዬ አስረድተዋል።

"አሜሪካ በዓለም ዙሪያ ያሉ ስልታዊ የተፈጥሮ ሃብቶችን ሁሉ በእኔ ቁጥጥር ስር መሆን አለባቸው ብላ ስለምታምን" ማንኛውም ሃብታም አገር ይህንን ስጋት ሊገነዘብ ይገባል።

አሜሪካ በአሁኑ ወቅት በኢራን ላይ ጥቃት እያደረሰች ቢሆንም፣ ሩሲያን የመበታተን እና ቻይናን የማዳከም እቅዷን እንዳልተወች ሃቢያሬምዬ ያምናሉ።

​ "ይህ በእውነቱ ለሩሲያ እና ለቻይና ማስጠንቀቂያ ነው። የኢራን ሽንፈት በማንኛውም ዋጋ መከላከል አለበት" ሲሉ ተንታኙ አስጠንቅቀዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0