ኪዬቭ ለድርድር ዝግጁ ባለመሆኗ ሩሲያ የልዩ ወታደራዊ ዘመቻዋን ግቦቿን በወታደራዊ መንገድ ታሳካለች - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ

ሰብስክራይብ

ኪዬቭ ለድርድር ዝግጁ ባለመሆኗ ሩሲያ የልዩ ወታደራዊ ዘመቻዋን ግቦቿን በወታደራዊ መንገድ ታሳካለች - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ

ማሪያ ዛካሮቫ በመግለጫቸው ያነሷቸው  ተጨማሪ ነጥቦች፦

​▪የአውሮፓ ሕብረት በቡቻ ክስተቶች ላይ እጃቸው አለበት ተብለው በሚጠረጠሩ የሩሲያ ዜጎች ላይ ሊጥለው ያሰበው ማዕቀብ፤ "የእብደት ስርዓት" እና በጤናማ አስተሳሰብ ላይ የሚደረግ ስላቅ ነው።

​▪ሩሲያ በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ውስጥ ያሉ ወገኖች በሙሉ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ ታቀርባለች።

​▪ሩሲያ ለኢራን ሰብአዊ ድጋፍ ማቅረቧን ትቀጥላለች።

​▪ሩሲያ በኢራን የሚገኘው የቡሸር የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ የተፈጸመውንና ኃላፊነት የጎደለውን ተቀባይነት የሌለው የሚሳኤል ጥቃት በጽኑ ታወግዛለች፤ ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ እና ከመላው ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ምላሽ ትጠብቃለች፡፡

​▪በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ ጥምረት ለመፍጠር የቀረበውን የአሜሪካ ተነሳሽነት የተቀበሉ አገራት፤ ራሳቸውን የጦርነቱ ተካፋይ እና የወረራው ተባባሪ ናቸው፡፡

​▪ደቡብ ኮሪያ የኔቶን "የዩክሬን ቅድሚያ ፍላጎቶች ዝርዝር" ተግባራዊ ለማድረግ የያዘችውን እቅድ ሩሲያ በቅርበት እየተከታተለች ነው፤ ሴኡል ለኪዬቭ ገዳይ መሳሪያዎችን ላለማቅረብ የገባችውን ቃል እንደምታከብርም ተስፋ ታደርጋለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0