የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡና ማኅበር የዓለም የቡና ዋጋ መቀነሱን ተከትሎ የዘርፉ ተዋናዮች ምርታቸውን በአስቸኳይ ለገበያ እንዲያቀርቡ አሳሰበ
18:16 18.03.2026 (የተሻሻለ: 18:34 18.03.2026)
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡና ማኅበር የዓለም የቡና ዋጋ መቀነሱን ተከትሎ የዘርፉ ተዋናዮች ምርታቸውን በአስቸኳይ ለገበያ እንዲያቀርቡ አሳሰበ
ማኅበሩ ከሁለት ቀናት በፊት ባወጣው አስቸኳይ መልዕክት፣ በአሁኑ ወቅት የዓለም የቡና ገበያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡
ምርት ሳይሸጥ በእጅ ላይ መቆየቱ ለከፋ የገንዘብ ኪሳራ ከመዳረጉ ባለፈ በሕግም ተጠያቂ ሊያደርግ እንደሚችል ማስጠንቀቁ ተዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን፣ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት የዓለም አቀፍ የቡና ገበያ ለውጥን እና የኢትዮጵያን የቡና ዘርፍ ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ የቡና አቅራቢዎች፣ ላኪዎች እና አርሶ አደሮች ያከማቹትን ቡና ሽያጩን በማፋጠን ወደ ማዕከላዊ ገበያ እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርቧል።
ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ የዓለም አቀፍ የቡና ዋጋ ከአራት ዶላር አካባቢ ወደ 2.80 ዶላር ዝቅ ያለ ሲሆን ዋጋው ይበልጥ ቀንሶ ወደ 2.50 ዶላር ሊወርድ እንደሚችል የሚጠቁሙ ግምቶች በዘርፉ ተዋንያን ላይ ተጨማሪ ጫና እየፈጠሩ መሆኑንም አክለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X