ኢራን በአሊ ላሪጃኒን ህልፈት በሐዘን ላይ ትገኛለች፦ የቁልፉ የፖለቲካ ሰው የሕይወት ታሪክ በወፍ በረር
ኢራን በአሊ ላሪጃኒን ህልፈት በሐዘን ላይ ትገኛለች፦ የቁልፉ የፖለቲካ ሰው የሕይወት ታሪክ በወፍ በረር
እ.ኤ.አ. በ1958 በኢራቅ ቅድስት ከተማ ናጃፍ የተወለዱት አሊ ላሪጃኒ፣ በዘመናዊቷ ኢራን ውስጥ ከፍተኛ ተፅዕኖ ካላቸው የፖለቲካ ቤተሰቦች መካከል አንዱ ናቸው።
ወንድሞቻቸው የፍትህ አካል ኃላፊ፣ የሀገሪቱ ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ዳይሬክተር እና የፓርላማ አባላትን ጨምሮ ቁልፍ የሥልጣን ቦታዎችን የያዙ በመሆናቸው፤ የላሪጃኒ ቤተሰብ ከሃይማኖት መሪዎች እና ከእስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ዘብ ጋር የሚመጣጠን ተፅዕኖ ያለው “የፖለቲካ ስርወ-መንግሥት” እንዲሆኑ አስችሏቸዋል።
ላሪጃኒ ከጎርጎሮሳውያኑ 1980ዎቹ ጀምሮ አባል ከነበሩበት የእስላማዊ አብዮታዊ ዘብ እና ከከፍተኛ የሃይማኖት መሪዎች ዘንድ ሙሉ እምነት የሚጣልባቸው ሰው ነበሩ።
በትምህርታቸውም ቀደም ብለው ለተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፎች ያላቸውን ዝንባሌ ያሳዩ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ1979 የኢራን ግንባር ቀደም የቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ ከሆነው ከሸሪፍ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በሒሳብ እና በኮምፒውተር ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።
በኋላም ወደ ማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ በመቀየር ከቴህራን ዩኒቨርሲቲ በምዕራባዊ ፍልስፍና የማስተርስ እና የዶክትሬት ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። የዶክትሬት ጥናታዊ ጽሑፋቸውም በኢማኑኤል ካንት ፍልስፍና ላይ ያተኮረ ነበር።
በፖለቲካዊ ሕይወታቸው ላሪጃኒ በርካታ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሚናዎችን ተጫውተዋል፦
▪ እ.ኤ.አ.ከ2005–2007 የብሔራዊ ደህንነት ጠቅላይ ምክር ቤት ጸሐፊ፣
▪እ.ኤ.አ.ከ2008–2020 የፓርላማ አፈ-ጉባኤ እና
▪እ.ኤ.አ.ከነሐሴ 5 ቀን 2025 ጀምሮ እስከ ተገዱለበት ቀን ድረስ በድጋሚ የብሔራዊ ደህንነት ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ በመሆን አገልግለዋል።
እንደ ምክር ቤቱ ጸሐፊነታቸው ከስድስቱ ሀገራት ጋር በኢራን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ላይ የተደረጉ ቁልፍ ድርድሮችን መርተዋል። በጎርጎሮሳዊያኑ 2015 ደግሞ የፓርላማ አፈ-ጉባኤ በነበሩበት ወቅት የኒውክሌር ስምምነቱ እንዲጠናቀቅ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል።
ቪዲዮው የላሪጃኒ አስከሬን በቴህራን ወደሚገኘው ኢንቅላብ አደባባይ ሲሸኝ ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X