ኢትዮጵያ የድንች የወጪ ንግዷን ወደ መካከለኛው ምስራቅ እና ጎረቤት ሀገራት እያሰፋች መሆኑ ተገለፀ
16:45 18.03.2026 (የተሻሻለ: 16:54 18.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የድንች የወጪ ንግዷን ወደ መካከለኛው ምስራቅ እና ጎረቤት ሀገራት እያሰፋች መሆኑ ተገለፀ
የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አንዳስታወቀዉ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ በተጨማሪ ለጅቡቲ፣ ለሶማሊያ እና ለሱዳን ጨምሮ ለዓለም አቀፍ ገበያ የድንች ምርት በስፋት እየተላከ ነው።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ንጉሴ ደቻሳ እንደገለጹት፣ ሀገሪቱ ያላት መጠነ ሰፊ ድንች የማምረት አቅም የገጠር ነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል እና የሥራ ዕድል ለመፍጠር ቁልፍ መሆኑን ገልጸዋል።
አክለውም፣ ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ሙሉ በሙሉ ለማግኘት የተቀነባበሩ ወይም እሴት የተጨመረባቸው የድንች ምርቶችን ወደ ውጭ መላክ አስፈላጊ መሆኑን መናገራቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X