ኢትዮጵያ ለሩሲያ አልሚዎች የኢንቨስትመን አማራጮቿን ያስተዋወቀችበት ፎረም በሞስኮ ተካሄደ
13:31 18.03.2026 (የተሻሻለ: 13:34 18.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ለሩሲያ አልሚዎች የኢንቨስትመን አማራጮቿን ያስተዋወቀችበት ፎረም በሞስኮ ተካሄደ
በሩሲያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሩሲያ ፌዴሬሽን የንግድና ዘርፍ ምክር ቤት ጋር በመተባበር በትናንትናው ዕለት የተካሄደው ይህ መድረክ፣ የሩሲያ ኩባንያዎችን በአካልና በበይነ-መረብ ያሳተፈ ነበር።
የፎረሙ ኩረት ኢትዮጵያ ቅድሚያ በምትሰጣቸው፦
በማኑፋክቸሪንግ፣
በግብርና፣
በግብርና ማቀነባበሪያ፣
በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ እና
በቱሪዝም ዘርፎች ያሉ ዕድሎችን በማስተዋወቅ ላይ ነበር።
የሩሲያ ፌዴሬሽን የንግድና ዘርፍ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ኢቫኖቪች ፓዳልኮ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።
በሩሲያ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ በበኩላቸው፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጥልቅ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በማንሳት የሩሲያ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ያለውን ሰፊ የኢንቨስትመንት አቅም እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል ሲል ኤምባሲው አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X