ጊኒ፣ ላይቤሪያ እና ሴራሊዮን የድንበር ደህንነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱጊኒ፣ ላይቤሪያ እና ሴራሊዮን የድንበር ደህንነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
ጊኒ፣ ላይቤሪያ እና ሴራሊዮን የድንበር ደህንነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.03.2026
ሰብስክራይብ

ጊኒ፣ ላይቤሪያ እና ሴራሊዮን የድንበር ደህንነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

​በኮናክሪ በተካሄደው የሦስትዮሽ የመሪዎች ጉባኤ ላይ፣ መሪዎቹ በጋራ ድንበሮቻቸው ላይ የሚታዩ የግጭት መንስኤዎችን መመርመራቸውንና ዓለም አቀፍ ሕግጋትን እንዲሁም ቀጣናዊ አሰራሮችን መሰረት ባደረገ ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ቃል መግባታቸውን የጊኒ ፕሬዝዳንት ማማዲ ዱምቡያ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

መሪዎቹ የደህንነት ትብብራቸውን በሚከተሉት መንገዶች ለማጠናከር ተስማምተዋል፦

በድንበር አካባቢዎች የጋራ ጥበቃን ማጠናከር፣

የመረጃ ልውውጥ ማድረግ እና

በአካባቢው ባለሥልጣናት እና በደህንነት ኃይሎች መካከል ፈጣን የኮሙኒኬሽን ስርዓት መዘርጋት።

​"ውጥረቶችን ለመከላከል፣ ውይይትን ለማቀላጠፍ እንዲሁም የየብስ እና የባህር ድንበሮችን የመለየትና የመከለል ሥራን ለማስቀጠል የድንበር ጉዳዮች የሚመለከታቸው የቴክኒክ ክፍሎች በአስቸኳይ እንዲገናኙ መመሪያ ተሰጥቷል" ሲል ጽሕፈት ቤቱ ገልጿል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱጊኒ፣ ላይቤሪያ እና ሴራሊዮን የድንበር ደህንነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
ጊኒ፣ ላይቤሪያ እና ሴራሊዮን የድንበር ደህንነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.03.2026
አዳዲስ ዜናዎች
0