የሉሙምባ ግድያ፦ የቀድሞው የቤልጂየም ዲፕሎማት ከ65 ዓመታት በኋላ ለፍርድ ሊቀርቡ ነው
11:32 18.03.2026 (የተሻሻለ: 11:34 18.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሉሙምባ ግድያ፦ የቀድሞው የቤልጂየም ዲፕሎማት ከ65 ዓመታት በኋላ ለፍርድ ሊቀርቡ ነው
የቤልጂየም የፍትሕ ሥርዓት አንድ ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ ደርሷል፤ በትናንትናው ዕለት ዕድሜያቸው 93 የሆኑት ኤቲየን ዳቪኞ "በጦር ወንጀል ተሳትፎ" ክስ ለፍርድ እንዲቀርቡ ተወስኗል።
ግለሰቡ የኮንጎውን መሪ ፓትሪስ ሉሙምባን ተገንጥላ ወደሄደችው ካታንጋ ክፍለ ሀገር ተላልፈው ሲሰጡ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል በሚል ተከስሰዋል። ሉሙምባ እ.ኤ.አ. ጥር 17 ቀን 1961 ግዛቲቱ ውስጥ በቤልጂየም ቅጥረኞች መገደላቸው ይታወሳል።
"በመጨረሻ ቤልጂየም ከታሪኳ ጋር ፊት ለፊት እየተጋፈጠች ነው" ሲሉ የነፃነት ታጋዩ የልጅ ልጅ መህዲ ሉሙምባ ተናግረዋል።
አንድ የአፍሪካ መሪ በተገደሉበት ወቅት የነበሩ የቅኝ ገዥ ኃይል ተወካይ ለሟቹ ግድያ ተጠያቂ እንዲሆኑ በወንጀል ችሎት ሲመረመር ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
ይግባኝ የማይቀርብበት ከሆነ፣ ይህ የፍርድ ሂደት በሚቀጥለው ዓመት ጥር ሊጀመር ይችላል። እ.ኤ.አ.በ2011 በቀረበው አቤቱታ ከተካተቱት 11 ሰዎች መካከል በሕይወት የተረፉት ብቸኛው ሰው የቀድሞው የአውሮፓ ኮሚሽነር ሲሆኑ፣ የቀረበባቸውን ክስ ግን ያስተባብላሉ።
ይሁን እንጂ፣ ከሳሾቻቸው እንደሚሉት ዳቪኞ "ለአስከፊ ዓላማ በተደራጀ የመንግሥት የወንጀል ተቋም" ውስጥ እንደ "አገናኝ" ነበሩ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X