የእንዶዴ ግንባታዎች የሎጂስቲክስ ሉዓላዊነታችንን በራስ አቅም የማረጋገጥ አዲስ ምዕራፍ ናቸው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

የእንዶዴ ግንባታዎች የሎጂስቲክስ ሉዓላዊነታችንን በራስ አቅም የማረጋገጥ አዲስ ምዕራፍ ናቸው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር

ተመስገን ጥሩነህ በትናንትናው ዕለት በኤኤምጂ - እንዶዴ የባቡር መሥመር እና የእንዶዴ ደረቅ ወደብ ማስፋፋያ ፕሮጀክቶች ላይ የመስክ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

የኤኤምጂ - እንዶዴ የባቡር መሥመር በሀገር በቀል የግል ኩባንያ ፋይናንስ የተደረገ የመጀመሪያው የባቡር መሠረተ ልማት መሆኑን በመጥቀስ ስለ ፕሮጀክቱ የሚከተሉትን ተናግረዋል፦

በልዩ ትኩረት ከተያዘለት ጊዜ ቀድሞ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

የሦስት ኪ.ሜ. ፕሮጀክቱ የገላን ኢንዱስትሪ ዞን ምርቶችን በቀጥታ ከባቡር መሥመሩ ጋር ያገናኛል፡፡

ምርቶች በፍጥነትና በተወዳዳሪ ዋጋ ለዓለም ገበያ እንዲቀርቡ ያስችላል።

በሌላ በኩል፣ የእንዶዴ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ የኮንቴነር ማከማቻ ዐቅም በ5 እጥፍ ማደጉን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ ጽፈዋል።

“የጭነት የማውረድና የመጫን መጫኛ ጊዜን ከ10 ሠዓት ወደ ሁለት ሠዓት ዝቅ በማድረግ የንግድ ሥርዓታችንን ያዘምናል፤ ፈጣን የሎጂስቲክስ አገልግሎትን ይፈጥራል።” ብለዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0