ሩሲያ እና ኬንያ የንግድ ልውውጣቸውን በሦስት እጥፍ ማሳደግ ይችላሉ ሲሉ የኬንያው ከፍተኛ ዲፕሎማት ገለፁ
20:37 17.03.2026 (የተሻሻለ: 20:44 17.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና ኬንያ የንግድ ልውውጣቸውን በሦስት እጥፍ ማሳደግ ይችላሉ ሲሉ የኬንያው ከፍተኛ ዲፕሎማት ገለፁ
የኬንያ የካቢኔ ዋና ጸሐፊ ሙሳሊያ ሙዳቫዲ በሞስኮ እያደረጉት ባለው መንግሥታዊ የሥራ ጉብኝት ወቅት ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደገለጹት፣ ሁለቱ አገራት አሁን ያለውን ጠንካራ አጋርነት ይበልጥ ለማሳደግ ጥሩ ዕድል አላቸው።
የአገሪቱ የውጭና ዳያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር ሆነው የሚያገለግሉት እኚሁ ባለሥልጣን፣ ከሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ከተወያዩ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት "ሩሲያ ከ62 ዓመታት በፊት ለነፃነታችንን ቀድመው እውቅና ከሰጡት አገራት መካከል አንዷ ነበረች" ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።
እንደ ሙዳቫዲ ገለጻ፣ ሩሲያ በሚከተሉት በርካታ ዘርፎች ከኬንያ ጋር "አብራ ተጉዛለች"፦
🟠 በጤና ጥበቃ፣
🟠በትምህርት፣
🟠 በግብርና፣
🟠በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT)፣
🟠 ከደኅንነት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች እና
🟠 በንግድ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X