- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

''ያልተበደረችውን ዕዳ የምትከፍለው አፍሪካ'':-የአየር ንብረት ለውጥ እና 'ዘመናዊ' ተብለው የቀረቡ የግብርና ወጥመዶች

''ያልተበደረችውን ዕዳ የምትከፍለው አፍሪካ'':- የአየር ንብረት ለውጥ እና 'ዘመናዊ' ተብለው የቀረቡ የግብርና ወጥመዶች
ሰብስክራይብ

"ዓለም ቀደም ሲል ከነበረው የአስተሳሰብ ዘይቤ በተለየ መንገድ ማሰብ ይኖርበታል። መሰረታዊ ነገሮች መለወጥ አለባቸው፤ ምክንያቱም አሁን ያለው ሁኔታ ፍትሃዊ ያልሆነና ዘላቂነት የሌለው ነው። ስለዚህ፣ የምዕራባውያን ዓለም ለአየር ንብረት ለውጥ ካደረጉት አስተዋጽኦ ጋር የሚመጣጠን በቂ ድጋፍ የማቅረብ ኃላፊነትን ሊወስዱ ይገባል፡፡" ሲሉ የግብርና ሳይንቲስት እና ተመራማሪ ፀደቀ አባተ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በክፍል አንድ የአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካን ግብርና እንዴት እየቀየረው እንደሆነና አፍሪካ ለዓለም አቀፉ የጋዝ ልቀት የምታበረክተው አስተዋጽዎ በጣም አነስተኛ ቢሆንም፣ ለምን የከፋውን ጫና ለመሸከም እንደተገደደች የግብርና ሳይንቲስት እና ተመራማሪ ከሆኑት ፀደቀ አባተ (ዶ/ር) ጋር ባደረግነው ቆይታ የዳሰስነው ሲሆን፤ በሁለተኛው ክፍል ደግሞ፣ የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ ከሆኑት ከዶ/ር ሩት ዳኛቸው ጋር በመሆን፣ በኢትዮጵያውያን ወጣቶች ዘንድ እየተስፋፋ የመጣውን የሱስ ተገዥነት እና የአእምሮ ጤና ቀውስ እንፈትሻለን፤ ለዚህም ዝምተኛ የህዝብ ጤና ተግዳሮት መንስኤ የሆኑትን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ስርዓታዊ ጫናዎችን በዝርዝር እንመለከታለን።

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0