የአሜሪካ ፀረ -ሽብር ማዕከል ኃላፊ በኢራን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት በመቃወም ከሥልጣናቸው ለቀቁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአሜሪካ ፀረ -ሽብር ማዕከል ኃላፊ በኢራን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት በመቃወም ከሥልጣናቸው ለቀቁ
የአሜሪካ ፀረ -ሽብር ማዕከል ኃላፊ በኢራን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት በመቃወም ከሥልጣናቸው ለቀቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.03.2026
ሰብስክራይብ

የአሜሪካ ፀረ -ሽብር ማዕከል ኃላፊ በኢራን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት በመቃወም ከሥልጣናቸው ለቀቁ

​አሜሪካን ከኢራን ጋር ወደ ግጭት ውስጥ ለመክተት የታለመ የሐሰት መረጃ ዘመቻ ሰለባ ሆናለች ሲሉ ጆ ኬንት ገልጸዋል።

​"በኢራን ላይ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በቅን ልቦና መደገፍ አልችልም" ብለዋል ኬንት።

​በተጨማሪም፣ ኬንት አገሪቱ በአሁኑ ወቅት እየተከተለችው ያለው መስመር እንዲቀየርና ወሳኝ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጥሪ አቅርበዋል፤ በሳቸው አስተሳሰብ ይህ ካልሆነ ግን አሜሪካ ውድቀትና ትርምስ ይጋረጥባታል።

​ ይህ እርምጃ የካቲት 21 ግጭቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ የተመዘገበ የመጀመሪያው ከፍተኛ የሥልጣን መልቀቂያ ነው።

ℹ የካቲት 21 ቀን አሜሪካ እና እስራኤል ቴህራንን ጨምሮ በኢራን ግዛት ውስጥ በሚገኙ የዒላማ ቦታዎች ላይ ጥቃት መፈጸም የጀመሩ ሲሆን፤ በወቅቱ የንብረት ውድመትና የሲቪል ሰዎች ጉዳት መድረሱ ተዘግቧል።

ኢራንም በእስራኤል ግዛት እንዲሁም በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ አጸፋዊ ጥቃቶችን እያደረሰች ትገኛለች።

​ዋሽንግተን እና ቴል አቪቭ የወታደራዊ ዘመቻውን መጀመር አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ፣ ጥቃቱ "ቅድመ ጥንቃቄ" (ሳይቀደሙ መቅደም) መሆኑንና በኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ምክንያት ስጋት በመኖሩ የተወሰደ እርምጃ እንደሆነ ገልጸዋል። ይሁን እንጂ፣ በአሁኑ ወቅት በኢራን ያለውን መንግሥት የመለወጥ ፍላጎት እንዳላቸው በይፋ እየገለጹ ይገኛሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0