የኢትዮጵያ የዲጂታል ፋይናንስ ግብይት በእጥፍ በመጨመር ከ18.5 ትሪሊዮን ብር በላይ ተሻግሯል – ብሔራዊ ባንክ
19:04 17.03.2026 (የተሻሻለ: 19:14 17.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የዲጂታል ፋይናንስ ግብይት በእጥፍ በመጨመር ከ18.5 ትሪሊዮን ብር በላይ ተሻግሯል – ብሔራዊ ባንክ
ይህ በ2017 ዓ.ም የበጀት የተመዘገበው ፈጣን መስፋፋት ለኦፕሬሽናል፣ ለሳይበር እና ከማጭበርበር ጋር ለተያያዙ ስጋቶች ያለውን ተጋላጭነት የጨመረ መሆኑን ባንኩ ባወጣው ሦስተኛውን የፋይናንስ መረጋጋት ሪፖርት አስታውቋል።
የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማትን፣ የሰው ኃይል አቅምን እና የስጋት አስተዳደር ማዕቀፎችን ማጠናከር ከጊዜ ወደ ጊዜ አስፈላጊ እየሆነ መምጣቱንም መግለጫው አትቷል።
የኢትዮጵያ የፋይናንስ ሥርዓት መጠነኛ የኢኮኖሚ እድገት መቀዛቀዝ፣ ቀጣይነት ያለው የጂኦፖለቲካዊ ውጥረት እና ውጫዊ ድንገተኛ ክስተቶች የታዩበት አስቸጋሪ የዓለም አቀፍ ሁኔታ ጫናዎች ቢኖሩም፦
በሀገሪቱ የነበሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አመልካቾች በበጀት ዓመቱ ግልጽ መሻሻል አሳይተዋል፡፡
የዋጋ ግሽበት እየቀነሰ የኢኮኖሚ እድገቱ መጠናከሩ ለፋይናንስ ተቋማት የተረጋጋ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡
ወደ አዎንታዊ እውነተኛ ወለድ ተመን ለሚደረገው ሽግግር ድጋፍ ከመስጠቱም በላይ የገንዘብ ፖሊሲው ውጤታማነት እንዲጨምር አድርጓል።
በሌላ በኩል፣ የባንክ ዘርፉ የተረጋጋ፣ ጥንካሬ ያለው እና ዝቅተኛ ስጋት ያለበት ሆኖ መቀጠሉን ብሔራዊ ባንክ አመላክቷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X