'አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግሮች በመፍታት ረገድ በግንባር ቀደምትነት ሊሰለፉ ይገባል' - የኬንያ ከፍተኛ ዲፕሎማት

ሰብስክራይብ

'አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግሮች በመፍታት ረገድ በግንባር ቀደምትነት ሊሰለፉ ይገባል' - የኬንያ ከፍተኛ ዲፕሎማት

የኬንያ ካቢኔ ዋና ጸሐፊ ሙሳሊያ ሙዳቫዲ ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደገለጹት፣ "ከአኅጉሪቱ ውጭ ካሉ ወዳጆቻችን የሚመጣው አጋርነት የእኛን ዓላማዎች ሊደግፍና ሊያጠናክር የሚገባው እንጂ፣ አፍሪካዊ መፍትሔዎችን የሚተካ ወይም የአፍሪካን ተነሳሽነት የሚቀማ መሆን የለበትም። ይልቁንም እኛ ራሳችን የምናደርገውን ጥረት የሚደግፍ ሊሆን ይገባል" ብለዋል።

​ሙዳቪዲ፣ "ስለ ሰላምና ደኅንነት ማውራት ካለብን፣ እንደ አፍሪካ አገራት ስለ ሰላምና ደኅንነት እንነጋገር" ብለዋል።

የአገሪቱ የውጭና ዳያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር ሙዳቫዲ አክለውም፣ "ከድንበሮቻችን ባሻገር የሚመጣ ጣልቃ ገብነት ካለ፣ ዓላማው እኛን መከፋፈል ሳይሆን የሰላም ግባችን እንድንመታ ሊረዳን ይገባል" ሲሉ አሳስበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0