በናይጄሪያ በትንሹ የ23 ሰዎችን ሕይወት ስለቀጠፈው እና 108 ሰዎችን ለጉዳት ስለዳረገው የሽብር ጥቃት እስካሁን የታወቁ መረጃዎች - ፖሊስ
17:25 17.03.2026 (የተሻሻለ: 17:34 17.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በናይጄሪያ በትንሹ የ23 ሰዎችን ሕይወት ስለቀጠፈው እና 108 ሰዎችን ለጉዳት ስለዳረገው የሽብር ጥቃት እስካሁን የታወቁ መረጃዎች - ፖሊስ
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ ተከታታይ ጥቃቶች ተፈጽመዋል። እንደ የአካባቢው ፖሊስ ገለጻ፣ በማይዱጉሪ ከተማ በሦስት የሕዝብ መገኛ ቦታዎች ማለትም በገበያ፣ በዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል መግቢያ እና በፖስታ ቤት አካባቢ የፍንዳታ ድምጾች ተሰምተዋል።
ፍንዳታዎቹ በአጥፍቶ ጠፊዎች ሳይፈጸሙ እንዳልቀሩ ፖሊስ ዘግቧል።
እንደ የአካባቢው ባለሥልጣናት ገለጻ፣ በአሁኑ ወቅት በቦርኖ ግዛት የጋራ የደህንነት ኃይሎች በማይዱጉሪ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ የጥበቃ ሥራ እያከናወኑ ይገኛሉ።
ℹ ማይዱጉሪ እ.ኤ.አ. በ2009 የቦኮ ሃራም ቡድን የተፈጠረባት ከተማ ናት። ቡድኑ እ.ኤ.አ. በ2015 ከገጠመው ሽንፈት በኋላ ለሁለት የተከፈለ ሲሆን፣ ይህም በምዕራብ አፍሪካ አይ.ኤስ.* እንዲመሠረት ምክንያት ሆኗል።
* በሩሲያ እና በሌሎች ሀገራት የታገደ አሸባሪ ድርጅት
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/4
© telegram sputnik_ethiopia

2/4
© telegram sputnik_ethiopia

3/4
© telegram sputnik_ethiopia

4/4
© telegram sputnik_ethiopia
1/4
© telegram sputnik_ethiopia
2/4
© telegram sputnik_ethiopia
3/4
© telegram sputnik_ethiopia
4/4
© telegram sputnik_ethiopia