ሁሉም የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የማሪታይም ሥልጠና ተቋማትን ሊያቋቁሙ መሆኑ ተዘገበ

ሰብስክራይብ

ሁሉም የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የማሪታይም ሥልጠና ተቋማትን ሊያቋቁሙ መሆኑ ተዘገበ

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ባሕር ዳር በሚገኘው የኢትዮጵያ የማሪታይም ሥልጠና ኢንስቲትዩት ብቻ ተወስኖ የቆየውን የትምህርት ዘርፍ በመላ ሀገሪቱ ለማስጀመር ዝግጅት እያደረጉ ነው ተብሏል፡፡

ይህ ለማሳካትም ውይይት እየተደረገ መሆኑን በመንግሥት እና የግል ዘርፍ አጋርነት የማሪታይም እና የሥራ ስምሪት ላይ የሚሠራው ዋይሲኤፍ ግሩፕ ዋና ሥራ አሰፈጻሚ ፍራንስ ጁበርት ለአገር ውስጥ የግል ሚዲያ ገልፀዋል፡፡

በ29 ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎችን የሚያሳትፈው ይህ ዕቅድ፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የመርከብ ኢንዱስትሪ ያላትን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ ነው።

በዘገባው ውስጥ የተካተቱ ተጨማሪ ነጥቦች፦

⭕ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በየዓመቱ 500 የሚጠጉ ተማሪዎችን በማሪታይም መርሃ ግብሮች ታሠለጥናለች።

⭕ አገሪቱ እስከ 8,000 የሠለጠኑ ባሕረኞች (መርከበኞች) አሏት።

⭕ የባሕረኞች ቁጥር በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ወደ 45,000 ለማሳደግ ግብ ተቀምጧል።

⭕ ተፈጻሚነቱ ቢያጠራጥርም በአንድ ክፍል ውስጥ በአማካይ 44 ተማሪዎችን የማሠልጠን እቅድ ተይዟል፡፡ 

⭕ የሥልጠናው መስፋፋት ከፍተኛ የውጭ በማስገኘት ለአገር ኢኮኖሚ እድገት አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ታልሟል፡፡ 

መረሃ ግብሩ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴርን ጨምሮ በበርካታ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች እና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትብብር የሚከናወን ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ማሪታይም ኢንስቲትዩት አስተባባሪነት ይመራል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0