ኢትዮጵያ ባለፉት አራት ዓመታት ከ18 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ስባለች - የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን
12:32 17.03.2026 (የተሻሻለ: 12:34 17.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ባለፉት አራት ዓመታት ከ18 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ስባለች - የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን
ይህ ዕድገት የተመዘገበው ከ2013 እስከ 2017 ዓ.ም ባሉት አራት ዓመታት ውስጥ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
በሀገሪቱ እየተተገበረ የሚገኘው አገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲጨምር እያደረገ ይገኛል ሲሉ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) በአዲስ አበባ በተካሄደ የኢንቨስትመንት ጉባኤ ላይ ተናግረዋል።
አክለውም፣ ነፃ የንግድ ቀጣናዎች ለውጭ ባለሀብቶች ምቹ የሆነ የሥነ-ምህዳር ዕድል መፍጠራቸውን ጠቁመው፣ የአዳዲስ ባለሀብቶች መግባት ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለቴክኖሎጂ ሽግግር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አስረድተዋል።
የሀገሪቱን ተፈጥሮአዊ ሀብቶች በቴክኖሎጂ በማልማት ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን ኮሚሽነሩ ማስረዳታቸውን መንግሥት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X