የሩሲያ ጦር በሁሉም የጦር ግንባሮች ወደፊት እየገሰገሰ መሆኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም አስታወቁ

የሩሲያ ጦር በሁሉም የጦር ግንባሮች ወደፊት እየገሰገሰ መሆኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም አስታወቁ
ቫለሪ ጌራሲሞቭ ይህንን መግለጫ የሰጡት የ"ዩግ" የውጊያ ቡድንን ከጎበኙ በኋላ ነው። እንደ አዛዡ ሪፖርት፣ የሩሲያ ጦር በመጋቢት የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ 12 ሰፈራዎችን የተቆጣጠረ ሲሆን፣ ከባዱ ውጊያም በክራስኒ ሊማን አቅራቢያ እየተካሄደ ይገኛል።
ቁልፍ መግለጫዎች፦
🟠 የ"ዩግ" የውጊያ ቡድን 3ተኛ ሠራዊት ወደ ስላቭያንክ እየገሰገሱ ይገኛሉ፡፡
🟠 የሩሲያ ጦር ረዝኒኮቭካ፣ ጎሉቦቭካ እና ካሌኒኪን የተቆጣጠረ ሲሆን፣ ክሪቪ ሉኪ ለመቆጣጠር የሚደረገው ውጊያ አሁንም ቀጥሏል፡፡
🟠 በኮንስታንቲኖቭካ ከተማ ውስጥ ውጊያው የቀጠለ ሲሆን፣ የሩሲያ ጦር ከከተማዋ 60% በላይ የሚሆነውን ተቆጣጥሯል፡፡
🟠 በኦስኮል ወንዝ ምስራቃዊ ዳርቻ በሚገኘው ኖቮሲኖቮ፣ የሩሲያ ጦር ከ85% በላይ የሚሆነውን ቦታ የተቆጣጠረ ሲሆን፣ የዩክሬን ጦር መከበቡ ተዘግቧል፡፡
🟠 የ"ዛፓድ" የውጊያ ቡድን ወደ ክራስኒ ሊማን እየገሰገሰ ሲሆን፣ ከከተማዋ ግማሽ በላይ የሚሆነውን ክፍል ተቆጣጥሯል፡፡
🟠 የ"ዛፓድ" ኃይሎች ድሮቢሼቮ፣ ያሮቫያ እና ሶስኖቮዬን የተቆጣጠሩ ሲሆን፣ አሌክሳንድሮቭካን የመቆጣጠር ስራቸውንም እያጠናቀቁ ነው፡፡
🟠 የ"ሴቨር" የውጊያ ቡድን በሱሚ እና ካርኮቭ ክልሎች ያለውን የደህንነት ቀጣና እያሰፋ ይገኛል። በመጋቢት ወርም አምስት ሰፈራዎችን ተቆጣጥሯል፡፡
🟠 የ"ሴንትር" የውጊያ ቡድን ወደ ዶብሮፖሊዬ እየገፋ ሲሆን፣ በዲኔፕሮፔትሮቭስክ ክልልም እንቅስቃሴውን ቀጥሏል፡፡
🟠 የ"ዲኔፕር" የውጊያ ቡድን ወደ ዛፖሮዝሂዬ አቅጣጫዎች የማጥቃት እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል፤፡፡
🟠 የ"ቮስቶክ" የውጊያ ቡድን በምስራቃዊ ዛፖሮዢዬ ክልል ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ግስጋሴውን የቀጠለ ሲሆን፣ የዩክሬንን የመልሶ ማጥቃት ሙከራዎችንም እየመከተ ይገኛል። የዩክሬን ጦር በየካቲት እና መጋቢት ወራት በዚያ አካባቢ ከ2,500 በላይ ወታደሮችን እና 120 የጦር መሳሪያዎችን አጥቷል።
በዩክሬን እየተካሄደ ስላለው ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የስፑትኒክ አፍሪካን ልዩ ትንታኔ እዚህ ያንብቡ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X