የባሪያ ንግድ ካሳ፦ አፍሪካ የምዕራባውያንን ሕግጋት እየተገዳደረች መሆኑን ኮት ዲቯራዊዉ ምሁር ገለጹ
10:04 17.03.2026 (የተሻሻለ: 10:14 17.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የባሪያ ንግድ ካሳ፦ አፍሪካ የምዕራባውያንን ሕግጋት እየተገዳደረች መሆኑን ኮት ዲቯራዊዉ ምሁር ገለጹ
"በአትላንቲክ የባሪያ ንግድ ምክንያት የአውሮፓ መንግስታትን ወደ ፍርድ ቤት ማቅረብ ውስብስብ ቢሆንም፣ ሙሉ በሙሉ የማይቻል ግን አይደለም" ሲሉ በፖለቲካ እና ማህበራዊ ፍልስፍና የዶክትሬት ዲግሪ ያላቸው ሚያን ቻርለስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የጂኦፖለቲካዊ ለውጥ ነጥብ
ይህ ተነሳሽነት አፍሪካ ከቀድሞ ቅኝ ገዥ ኃይላት ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ ሚዛናዊ ለማድረግ ያላትን ፍላጎት የሚያንፀባርቅ መሆኑን ሚያን ቻርለስ አጽንኦት ሰጥተውበታል።
ታሪክን የውይይት ማዕከል የሚያደርግ፣ ነገር ግን ግንኙነትን የማይበጣጥስ "የትውዝታ ዲፕሎማሲ" በጋራ ጥቅሞች ላይ በሚደረጉ ውይይቶች እንደ ድርድር መሳሪያ ያገለግላል ብለዋል።
⁉ እንዲህ ያለው ሕጋዊ እርምጃ ቢሳካስ?
እንደ ባለሙያው ገለጻ፣ የካሳ ክፍያው በሦስት መልኩ ሊከናወን ይችላል፦
◾ተምሳሌታዊ፦ ይፋዊ ዕውቅና መስጠት፤
◾ፋይናንስ ተኮር፦ የካሳ ፈንድ ማቋቋም እና
◾መዋቅራዊ፦ በትምህርት እና በመሰረተ ልማት ላይ ኢንቨስት ማድረግ።
"ካሳዎች አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር በቀጥታ ገንዘብ በመስጠት ሁኔታ መልክ አይፈፀሙም፤ " ይልቁንም ዓላማቸው "አዲስ ግንኙነትን በጋራ መገንባት" ላይ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X