በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፉጃይራ የነዳጅ ተቋማት የኢንዱስትሪ ቀጣና ላይ የተፈፀመ የድሮን ጥቃት ቃጠሎ አስከተለ
19:15 16.03.2026 (የተሻሻለ: 19:24 16.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፉጃይራ የነዳጅ ተቋማት የኢንዱስትሪ ቀጣና ላይ የተፈፀመ የድሮን ጥቃት ቃጠሎ አስከተለ
የሲቪል መከላከያ ሠራዊት ቡድን ወዲያውኑ ቃጠሎውን ለማጥፋት እርምጃ የጀመረ ሲሆን አሁን ላይ እሳቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሠራ እንደሚገኝ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ገልፀዋል።
ቀደም ሲል የአየር መከላከያ ድሮን ተመትቶ ስብርባሪው በፎይዝ (FOIZ) የኢንዱስትሪ ቀጣና ላይ በማረፉ ከፍተኛ ቃጠሎ መድረሱን ባለሥልጣናት ገልጸው ነበር፡፡
ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኙት ተንቀሳቃሽ ምሥሎች፦
1 - የነዳጅ ማከማቻ ተቋማት በቃጠሎ ሲጋዩ፣ መጋቢት 5፣
2 - ዛሬ ጠዋት በፉጃይራ ሰማይ ላይ የተነሳውን ጢስ ያሳያሉ፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia