https://amh.sputniknews.africa
የባሕረ ሰላጤው ሀገራት በአሜሪካ እና በኢራን ግጭት ውስጥ ያልገቡት ከስታራቴጂካዊ ውሳኔ ተነስተው ነው - ኢራቃዊ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር
የባሕረ ሰላጤው ሀገራት በአሜሪካ እና በኢራን ግጭት ውስጥ ያልገቡት ከስታራቴጂካዊ ውሳኔ ተነስተው ነው - ኢራቃዊ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር
Sputnik አፍሪካ
የባሕረ ሰላጤው ሀገራት በአሜሪካ እና በኢራን ግጭት ውስጥ ያልገቡት ከስታራቴጂካዊ ውሳኔ ተነስተው ነው - ኢራቃዊ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁርየባሕረ ሰላጤው ሀገራት አጸፋዊ እርምጃ ከመውሰድ የተቆጠቡት፤ በግዛታቸው ላይ ለደረሱ ጥቃቶች አሜሪካ ወይም እስራኤል... 16.03.2026, Sputnik አፍሪካ
2026-03-16T19:05+0300
2026-03-16T19:05+0300
2026-03-16T19:14+0300
sputnik africa
telegram sputnik_ethiopia
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/03/10/3565045_0:42:800:492_1920x0_80_0_0_4785852a1cf4adee3bf7ba21e4c5af21.jpg
የባሕረ ሰላጤው ሀገራት በአሜሪካ እና በኢራን ግጭት ውስጥ ያልገቡት ከስታራቴጂካዊ ውሳኔ ተነስተው ነው - ኢራቃዊ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁርየባሕረ ሰላጤው ሀገራት አጸፋዊ እርምጃ ከመውሰድ የተቆጠቡት፤ በግዛታቸው ላይ ለደረሱ ጥቃቶች አሜሪካ ወይም እስራኤል እጃቸው እንዳለበት የሚጠቁም መረጃ ስለደረሳቸው እንደሆነ የሚገልጹ ዘገባዎች ወጥተዋል፡፡ ለስፑትኒክ አስተያየታቸውን የሰጡት አብዱል ማሊክ አል-ሁሴኒ፤ በርካታ የባሕረ ሰላጤው ሀገራት ቀድሞውኑ በወታደራዊ እና በኢኮኖሚ ተቋሞቻቸው ላይ በኢራን የተሰነዘሩ ጥቃቶች እንዳስተናገዱ በማንሳት፤ መላምቱን ውድቅ አድርገውታል። እንደ ተንታኙ ገለጻ፤ የባሕረ ሰላጤው መንግሥታት በወቅታዊ ትንተናዎች ላይ ተመስርተው ነው ውሳኔው ላይ የደረሱት። እነዚህ ሀገራት ጦርነቱ ሲጀመር የውሳኔ አካል አልነበሩም፤ ቀደም ሲልም ግጭቱ እንዳይባባስ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ሲጥሩ ቆይተዋል። የላቁ የደህንነት መረጃ መከታተያ ሥርዓቶቻቸው፣ ከምዕራባውያን አጋሮቻቸው ጋር ያላቸው የጸጥታ ትብብር እና ሀገራዊ መረጋጋትን የመጠበቅ ፍላጎታቸውም ለውሳኔያቸው ትልቅ ሚና ተጫውቷል ብለዋል።አል-ሁሴኒ አክለውም፤ "በተለይም በተቃራኒው ወገን ያለችው ኢራን ከመሆኗ አንጻር እንዲሁም የእነዚህ ሀገራት ፖለቲካዊ እና የጸጥታ ሁኔታ ከማኅበረሰቦቻቸው ሰላም እና ብልጽግና ጋር ታክሎ፤ ሊራዘም በሚችል ጦርነት ውስጥ ላለመግባት ለመወሰን በቂ ምክንያቶች ናቸው" ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2026
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/03/10/3565045_45:0:756:533_1920x0_80_0_0_5b4c616a89f58448ab2f3d9684da3326.jpgSputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
የባሕረ ሰላጤው ሀገራት በአሜሪካ እና በኢራን ግጭት ውስጥ ያልገቡት ከስታራቴጂካዊ ውሳኔ ተነስተው ነው - ኢራቃዊ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር
19:05 16.03.2026 (የተሻሻለ: 19:14 16.03.2026) የባሕረ ሰላጤው ሀገራት በአሜሪካ እና በኢራን ግጭት ውስጥ ያልገቡት ከስታራቴጂካዊ ውሳኔ ተነስተው ነው - ኢራቃዊ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር
የባሕረ ሰላጤው ሀገራት አጸፋዊ እርምጃ ከመውሰድ የተቆጠቡት፤ በግዛታቸው ላይ ለደረሱ ጥቃቶች አሜሪካ ወይም እስራኤል እጃቸው እንዳለበት የሚጠቁም መረጃ ስለደረሳቸው እንደሆነ የሚገልጹ ዘገባዎች ወጥተዋል፡፡ ለስፑትኒክ አስተያየታቸውን የሰጡት አብዱል ማሊክ አል-ሁሴኒ፤ በርካታ የባሕረ ሰላጤው ሀገራት ቀድሞውኑ በወታደራዊ እና በኢኮኖሚ ተቋሞቻቸው ላይ በኢራን የተሰነዘሩ ጥቃቶች እንዳስተናገዱ በማንሳት፤ መላምቱን ውድቅ አድርገውታል።
እንደ ተንታኙ ገለጻ፤ የባሕረ ሰላጤው መንግሥታት በወቅታዊ ትንተናዎች ላይ ተመስርተው ነው ውሳኔው ላይ የደረሱት። እነዚህ ሀገራት ጦርነቱ ሲጀመር የውሳኔ አካል አልነበሩም፤ ቀደም ሲልም ግጭቱ እንዳይባባስ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ሲጥሩ ቆይተዋል።
የላቁ የደህንነት መረጃ መከታተያ ሥርዓቶቻቸው፣ ከምዕራባውያን አጋሮቻቸው ጋር ያላቸው የጸጥታ ትብብር እና ሀገራዊ መረጋጋትን የመጠበቅ ፍላጎታቸውም ለውሳኔያቸው ትልቅ ሚና ተጫውቷል ብለዋል።
አል-ሁሴኒ አክለውም፤ "በተለይም በተቃራኒው ወገን ያለችው ኢራን ከመሆኗ አንጻር እንዲሁም የእነዚህ ሀገራት ፖለቲካዊ እና የጸጥታ ሁኔታ ከማኅበረሰቦቻቸው ሰላም እና ብልጽግና ጋር ታክሎ፤ ሊራዘም በሚችል ጦርነት ውስጥ ላለመግባት ለመወሰን በቂ ምክንያቶች ናቸው" ብለዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X