"የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን በኢራንና እስራኤል ግጭት ዙሪያ የሚያቀርቡት ዘገባ ሚዛናዊነት የጎደለውና የተዛባ ነው” - የጋዜጠኝነት መምህር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ"የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን በኢራንና እስራኤል ግጭት ዙሪያ የሚያቀርቡት ዘገባ ሚዛናዊነት የጎደለውና የተዛባ ነው” - የጋዜጠኝነት መምህር
የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን በኢራንና እስራኤል ግጭት ዙሪያ የሚያቀርቡት ዘገባ ሚዛናዊነት የጎደለውና የተዛባ ነው” - የጋዜጠኝነት መምህር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.03.2026
ሰብስክራይብ

"የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን በኢራንና እስራኤል ግጭት ዙሪያ የሚያቀርቡት ዘገባ ሚዛናዊነት የጎደለውና የተዛባ ነው” - የጋዜጠኝነት መምህር

በወሎ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ሥነ-ተግባቦት መምህር ኢብራሂም ሰይድ፤ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን በመካከለኛው ምሥራቅ ያለውን ወቅታዊ ግጭት የሚዘግቡበት መንገድ "የተመረጡ መረጃዎችን ብቻ በማቅረብ" እና የአንድን ወገን ትርክት በማስቀደም ላይ የተመሠረተ ነው ሲሉ ተችተዋል።

ተቋማቱ የምዕራባውያንን ጥቅም የሚያስጠብቅ ትርክት ለመገንባት ሆን ብለው ወሳኝ መረጃዎችን እንደሚሸፍኑ ወይም ሁኔታዎችን በሚፈልጉት መንገድ ቀርጸው እንደሚያቀርቡ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

"ይህ ሆነ ተብሎ የሚመራ የተቀናጀ ፕሮጀክት፤ በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በአፍሪካ አልፎ ተርፎም በሩሲያና ምሥራቅ አውሮፓ ላይ ተግባራዊ ሲያደርጉት ይታያል" ብለዋል፡፡

ሚዲያዎቹ በተደራሽነታቸው ልክ ብዙኃኑን ከማገልገል ይልቅ መርጦ አልቃሽ በመሆን የዘርፉን ቁልፍ መርህ እየሳቱ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

"በጋዛ ከ200 በላይ ጋዜጠኞች ተገድለዋል። በኢራን በሚገኝ አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ በደረሰ ጥቃት ሴት ተማሪዎች ተጨፍጭፈዋል። የምዕራባውያን ሚዲያዎች ግን ይህንን ላይ ላዩንና በሚያሳዝን መንገድ ነው የዘገቡት። ይህ የሚያሳየው ፍትሕ እንደሌለ ነው" ብለዋል።

መገናኛ ብዙኃኑ ሚዛናዊነት በጎደለው አሠራራቸው ከቀጠሉ በዘመኑ የሚዲያ አማራጮች ሊተኩ እንደሚችሉም መምህሩ አስጠንቅቀዋል፡፡

"እንደ ሲኤንኤን፣ ፎክስ ኒውስ፣ ቢቢሲ እና ሮይተርስ ያሉ ተቋማት በአቋማቸው አይታመኑም። ግጭቶችን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ማስተናገድ ካልቻሉ በተፅዕኖ ፈጣሪ የማኅበራዊ ሚዲያ አንቀሳቃሾች ይተካሉ።"

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0