በአዲስ አበባ የሕንፃ ግንባታ ሠራተኞችን ደኅንነት ለመጠበቅ ያለመ አስገዳጅ አሠራር ተግባራዊ ሊሆን ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበአዲስ አበባ የሕንፃ ግንባታ ሠራተኞችን ደኅንነት ለመጠበቅ ያለመ አስገዳጅ አሠራር ተግባራዊ ሊሆን ነው
በአዲስ አበባ የሕንፃ ግንባታ ሠራተኞችን ደኅንነት ለመጠበቅ ያለመ አስገዳጅ አሠራር ተግባራዊ ሊሆን ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.03.2026
ሰብስክራይብ

በአዲስ አበባ የሕንፃ ግንባታ ሠራተኞችን ደኅንነት ለመጠበቅ ያለመ አስገዳጅ አሠራር ተግባራዊ ሊሆን ነው

የአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን በግንባታ ቦታዎች ላይ የሚከሰቱ አደጋዎችንና የሕይወት መጥፋትን ለመከላከል አስገንቢዎች የሠራተኞችን ደኅንነት የሚቆጣጠር ባለሙያ እንዲቀጥሩ የሚያስገድድ መመሪያ እያዘጋጀ መሆኑን አስታውቋል።

17 ነጥቦችን የያዘው መመሪያው ማንኛውም ሕንፃ የሚያስገነባ አካል ልክ እንደ ኮንትራክተርና አማካሪ ሁሉ፤ የሠራተኞችን ደኅንነት የሚከታተል በዘርፉ የሠለጠነ ባለሙያ እንዲመድብ ያስገድዳል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም የግንባታ አካባቢዎች በደኅንነት መረብ እንዲሸፈኑ፣ ሠራተኞች የራስ መከላከያ፣ የደህንነት ጫማ፣ ጓንትና አንጸባራቂ ልብስ መልበሳቸውን በግዴታ የሚያስቀምጡ አሠራሮች በመመሪያው ተካተዋል።

‍ባለሥልጣኑ በዚህ ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት 2,000 ባለሙያዎችን ለማሠልጠን አቅዶ እስካሁን ከ800 በላይ ባለሙያዎችን እንዳሠለጠነ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

ባለፉት ሦስት ዓመታት ብቻ በግንባታ ጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት 142 ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ በዘገባው ተመላክቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0