የአፍሪካ ሀገራት ትብብር ለአኅጉሪቱ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ወሳኝ ነው - አሜሪካዊ ፕሮፌሰር
20:10 15.03.2026 (የተሻሻለ: 20:14 15.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሀገራት ትብብር ለአኅጉሪቱ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ወሳኝ ነው - አሜሪካዊ ፕሮፌሰር
የኢኮኖሚ ባለሙያው ፋደል ካቡብ፤ የአፍሪካ ሀገራት በመካከለኛው ምስራቅ ካለው ቀውስ ጋር ተያይዞ የራሳቸውን ገንዘብ ለመጠበቅ እና መሠረታዊ ምርቶችን ለማግኘት የኢኮኖሚ ፖሊሲዎቻቸውን በአኅጉራዊ ደረጃ
ማቀናጀት አለባቸው ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
አንዱ አፋጣኝ እርምጃ አኅጉር አቀፍ የጋራ ግዢ ሥርዓት መፍጠር እንደሆነ ገልጸዋል። ሀገራት ለብቻቸው ከመደራደር ይልቅ በአፍሪካ መንግሥታት ኅብረት እንደ ማዳበሪያ፣ የመስኖ መሣሪያዎች እና የሕክምና ቁሳቁሶችን የመሳሰሉ አስፈላጊ ምርቶችን በጋራ መግዛት ይችላሉ ብለዋል።
ይህ አካሄድ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ዋጋ ከ5-10 በመቶ ሊቀንስ ይችላል። ይህም ለመሠረተ-ልማት፣ ለኃይል ሥርዓቶች፣ ለትምህርት እና ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያ የሚውሉ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ለማዳን ያስችላል ሲሉ አክለዋል።
"ፓን-አፍሪካኒዝም የለውጥ ኢኮኖሚ ነው" ሲሉ አጽንኦት የሰጡት ፕሮፌሰሩ፤ የትኛውም የአፍሪካ ሀገር በራሱ በኢንዱስትሪ ሊበለጽግ እንደማይችል አንስተዋል።
ካቡብ አክለውም የነዳጅ ዋጋ መናር ቀድሞውኑ በዕዳ የተዘፈቁ የአፍሪካ ሀገራት ዕዳቸውን መክፈል ወደማይችሉበት ደረጃ ሊያደርሳቸው እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
አለመረጋጋትን ለመከላከልም የአፍሪካ እና የደቡባዊው ዓለም ተበዳሪዎች ጥምረት እንዲመሰረት ሐሳብ አቅርበዋል።
የአፍሪካ ጂኦፖለቲካዊ ተፅዕኖ በአንድነት ላይ የተመሠረተ ነው ያሉት ባለሙያው "የአፍሪካ አኅጉር የጂኦፖለቲካዊ ተፅዕኖ አቅም ሊባል የሚችለው በአኅጉር ደረጃ ሲተገበር ብቻ ነው" ሲሉ ሀሳባቸውን ደምድመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X