በመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ታሪክ ከፍተኛ ነጥብ በማምጣት የሁለት ዋንጫዎችና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነችውን ወጣት ይተዋወቁ
18:25 15.03.2026 (የተሻሻለ: 18:34 15.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ታሪክ ከፍተኛ ነጥብ በማምጣት የሁለት ዋንጫዎችና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነችውን ወጣት ይተዋወቁ
ወጣት ሊና ወዩ ገና ትባላለች፤ ገና ዩኒቨርስቲውን ስትረግጥ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በክብር ቦርድ ላይ የተለጠፉ ተማሪዎችን ስታይ መነሳሳት እንደተፈጠረባት ትናገራለች።
"እኔም ስሜን ከፍ በማድረግ በዚህ ቦርድ ላይ ፎቷቸው ከሚለጠፍላቸው ተማሪዎች ተርታ መሆን አለብኝ" ስትልም ለራሷ ቃል ገባች።
ወጣት ሊና ወዩ ለራሷ የገባችውን ቃል ሳትስት በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቃለች።
ከማርኬቲንግ ትምህርት ክፍል 3.98 ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ከዩኒቨርሲቲው ሴት ተሸላሚዎች እንዲሁም ከአጠቃላይ ተማሪዎች አንደኛ በመሆን የሁለትዮሽ ዋንጫ አሸናፊና የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች።
ተማሪዋ ያስመዘገበችውን ከፍተኛ ውጤት ተከትሎ ከእውቅናው በተጨማሪ ዩኒቨርሲቲውን የመቀላቀል ዕድል እንዳገኘች የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X