ኢትዮጵያ የሥነ-ምኅዳር ደህንነትን ማስጠበቅና ምርታማነትን ማሳደግ ላይ ያተኮሩ ብሔራዊ ስትራቴጂዎችን ይፋ አደረገች
17:15 15.03.2026 (የተሻሻለ: 17:24 15.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የሥነ-ምኅዳር ደህንነትን ማስጠበቅና ምርታማነትን ማሳደግ ላይ ያተኮሩ ብሔራዊ ስትራቴጂዎችን ይፋ አደረገች
በግብርና ሚኒስቴር ይፋ የተደረጉት ስትራቴጂዎች የብሔራዊ ጥምር ደን እርሻ ልማትና ብሔራዊ የሥነ-ምህዳር ስትራቴጂዎች ናቸው።
የግብርና ሚኒስትር ደኤታ ፕሮፌሰር እያሱ ኤሊያስ፤ ብሔራዊ የሥነ-ምኅዳር ስትራቴጂው በአፈር ጤንነት ጥበቃ፣ በውሃ አጠቃቀምና ብዝኅ ህይወት ደኅንነትን በማስጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል።
ሁለቱ ብሔራዊ ስትራቴጂዎች የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነትና የመሬት ለምነት በማሻሻል የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ ተብሏል።
ብሔራዊ የአግሮ-ኢኮሎጂ ስትራቴጂ በፈረንጆች ዘመን አቆጣጠር ከ 2026-2040 ብሔራዊ የአግሮ-ፎሪስትሪ ስትራቴጂው ደግሞ ከ 2026-2035 ሥራ ላይ እንደሚውል የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X