በአዲስ አበባ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ክፍያ ላይ ጭማሪ ተደረገ
14:59 15.03.2026 (የተሻሻለ: 15:04 15.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአዲስ አበባ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ክፍያ ላይ ጭማሪ ተደረገ
አዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ ከመጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።
በአዲሱ የአገልግሎት ክፍያ እንደ ጉዞው ርቀት፦
በሚኒባስ፦ ከ5 ብር እስከ 10 ብር፣
በሚድባስ፦ ከ5 ብር እስከ 10 ብር፣
በከተማ አውቶብስ አገልግሎት፦ ከ5 እስከ 20 ብር ጭማሪ ተደርጓል።
ቢሮው አያይዞም የባጃጅ ትራንስፖርት ታሪፍ በሁሉም መስመሮች 10 ብር መሆኑን ገልጿል።
የትራንስፖርት ክፍያ ጭማሪው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያ ተከትሎ የመጣ መሆኑ ተጠቁሟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X