ትራምፕ ‘የስምምነት ነጥቦች በቂ አይደሉም’ በማለት የኢራንን ስምምነት ለጊዜው ውድቅ እንዳደረጉ ገለፁ
14:11 15.03.2026 (የተሻሻለ: 14:14 15.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ትራምፕ ‘የስምምነት ነጥቦች በቂ አይደሉም’ በማለት የኢራንን ስምምነት ለጊዜው ውድቅ እንዳደረጉ ገለፁ
ዶናልድ ትራምፕ ለኤንቢሲ በስልክ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፤ ኢራን አሜሪካ እና እስራኤል የከፈቱባት ጦርነት እንዲቆም ለመደራደር ፈቃደኛ መሆኗን ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ፤ ለእሳቸው የቀረቡት ነጥቦች ስምምነት ለመፈጸም በቂ አይደሉም።
“ስምምነቱን ማድረግ አልፈልግም፤ ምክንያቱም ነጥቦቹ በቂ አይደሉም። የትኛውም ስምምነት 'በጣም ጠንካራ' መሆን አለበት" ብለዋል።
ስምምነቱ ምን ማካተት እንዳለበት ሲጠየቁ፤ “ይህንን ለመናገር አልፈልግም” በማለት ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
ትራምፕ ኢራን ለአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራትን ኢላማ በማድረግ ምላሽ መስጠቷ የጠበቁት እንዳልነበርም አክለዋል።
በተጨማሪም አሜሪካ ቅዳሜ በካርግ ደሴት ላይ የሰነዘረችው ጥቃት አብዛኛውን የደሴቲቱን ክፍል “ሙሉ በሙሉ ደምስሶታል” ያሉ ሲሆን “ለደስታ ያህል ተጨማሪ ድብደባ ልናካሂድ እንችላለን” ብለዋል።
የቀጣናው ውጥረት በማየሉ ምክንያት የዓለም የነዳጅ ዋጋ መናሩን ተከትሎ አሜሪካ የሆርሙዝ ሰርጥን ደህንነት ለመጠበቅ ከ “በርካታ ሀገራት” ጋር በዕቅድ ላይ እየሠራች መሆኑን ገልጸዋል።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ፤ ወሳኙ የነዳጅ ማጓጓዣ መስመር የሚዘጋው “ጥቃት ለሚሰነዝሩብን ብቻ” ነው ሲሉ በድጋሚ መግለጻቸው የሚታወስ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X