አውሮፓውያን የተሳሳተ ስሌት ተከትለዋል፤ "ያለ ሩሲያ መዝለቅ አይችሉም" - ሶሪያዊ የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአውሮፓውያን የተሳሳተ ስሌት ተከትለዋል፤ "ያለ ሩሲያ መዝለቅ አይችሉም" - ሶሪያዊ የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪ
አውሮፓውያን የተሳሳተ ስሌት ተከትለዋል፤ ያለ ሩሲያ መዝለቅ አይችሉም - ሶሪያዊ የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.03.2026
ሰብስክራይብ

አውሮፓውያን የተሳሳተ ስሌት ተከትለዋል፤ "ያለ ሩሲያ መዝለቅ አይችሉም" - ሶሪያዊ የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪ

የአውሮፓ ኅብረት ኢኮኖሚውን "ለዩክሬን የሽንፈት ግጭት አገልግሎት" እንዲውል ማድረጉ "ስህተት ሆኖ በመገኘቱ ለበርካታ ቀውሶች ተዳርጓል" ሲሉ ኢያስ አል-ከቲብ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

"አውሮፓ ይህንን የተረዳችው በጣም ዘግይታ ነው" ሲሉም አክለዋል።

እንደ ተንታኙ ገለጻ፤ ሩሲያ ግጭቱ ወደ ወታደራዊ ምዕራፍ ከመሸጋገሩ በፊት ቀድማ የኢኮኖሚ ስትራቴጂዋን አዘጋጅታለች።

"ሩሲያ ውስጣዊ መረጋጋቷን፣ የገንዘቧን ጥንካሬ እና የነዳጅ ወጪ ንግዷን አስጠብቃ ስትቆይ፤ በተቃራኒው ከእሷ ጋር ግንኙነታቸውን ያቋረጡ ሀገራት ግን ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።"

በኃይል ቀውስ የተመታው ምዕራባዊው ዓለም፤ አሁን ላይ ማዕቀቦች እንዲነሱ በዝምታ እየጠየቀ ይገኛል። ከዚህም በላይ አውሮፓ ኅብረት ገለልተኝነቱን አጥቶ የመወሰን አቅሙን ለዋሽንግተን አሳልፎ ሰጥቷል ሲሉ ተንታኙ ገልጸዋል።

"ይህም ከአውሮፓ አቅም ማጣት ጋር ተያይዞ ወደማይጠቅም ግጭት እና ተገቢ ያልሆነ ፍጥጫ ውስጥ ከቶታል።"



በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0